የሳውዲ አረቢያ እና የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች በረመዳን ወቅት ለመገናኘት ማቀዳቸው ተገለፀ፡፡ሳውዲ እና ኢራን በቅርቡ ከሰባት ዓመታት የቆየ ቁርሾ በኃላ፣ የሰላም ስምምነት መፈራረማቸው…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/WMi0Iozm0vuB9yJK6szG7X1CtJ_72-Ag8f8H9hC0t6Qm5uv62mJH8Iw1sfeXUalQbeaKQpuXu-MmHRILG-ZoNX_Mkjf-A6T4AulG0qvYbbT_2ZBphkFHOrZRnyt0Ds93EuhQVUFHfyBmG5zHJGJGR3pADyXuZZGq-FdaEj4Zm8b0U2TgRuWqWHmwxnrVC3mFOVHDbO-na7C1riUfR1RaHlEZTsp0t0oOGHiHANiaVBG9PSALc4dHokJbELNfU8L54KcTQc9kTSfSvxNukrCdFJyDqW0J0qmIRX1rPXcz_LCoSJQkulduMZ41u6asjY1ufH2uKLGza8GhQgzGURLbPw.jpg

የሳውዲ አረቢያ እና የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች በረመዳን ወቅት ለመገናኘት ማቀዳቸው ተገለፀ፡፡

ሳውዲ እና ኢራን በቅርቡ ከሰባት ዓመታት የቆየ ቁርሾ በኃላ፣ የሰላም ስምምነት መፈራረማቸው ይታወቃል፡፡

የሁለቱ ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች በቻይና አደራዳሪነት የፈረሙት የሰላም ስምምነት ለመተግበር ቅዱሱ የረመዳን ወር ሳያልቅ ተገናኝተው ለመወያየት አቅደዋል ተብሏል፡፡

የሳወዲው ፕሬስ ኤጀንሲ ኤስ ፒ ኤ እንደገለፀው፣በሳምንት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ የስልክ ውይይት ያደረጉት፣የሳውዲው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ልዑል ፋይሰል ቢን ፋርሃን እና የኢራኑ አቻቸው ሆሲን አሚር አብዱልሃኒ በስምምነቱ መሰረት ተገናኝተው ለመናጋገር መወሰናቸው ታውቋል፡፡

ዘገባው ሚኒስትሮቹ መቼ እና የት እንደሚገናኙ የጠቀሰው ነገር ባይኖርም፣ በሚቀጥሉት ሶስት ሳምንታት ውስጥ ሊገናኙ ይችላሉ የሚል ተስፋ እንዳለ መረጃው ጠቅሟል፡፡

በአቤል ደጀኔ

መጋቢት 18 ቀን 2015 ዓ.ም

ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራምና የዩቲዩብ ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ!

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን

Source: Link to the Post

Leave a Reply