የሳዑዲ ዓረቢያን የመኖሪያ ፈቃድ ተላልፈዋል በሚል ላለፉት ሳምንታት በሪያድ ፖሊስ ጣቢያዎች የቆዩ 82 ዜጎች ከእስር ተፈቱ

የሳዑዲ ዓረቢያን የመኖሪያ ፈቃድ ተላልፈዋል በሚል ላለፉት ሳምንታት በሪያድ ፖሊስ ጣቢያዎች የቆዩ 82 ዜጎች ከእስር ተፈቱ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሳዑዲ ዓረቢያን የመኖሪያ ፈቃድ ተላልፈዋል በሚል ላለፉት ሳምንታት ከልጆቻቸው ጋር ተይዘው ሪያድ ባሉ ፖሊስ ጣቢያዎች የቆዩ 82 ዜጎች እንዲፈቱ አደረገ።

እነዚህ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በከተማው ውስጥ በሚገኙ 5 ፖሊስ ጣቢያዎች በጊዜያዊነት ከሶስት ሳምንታት በላይ እንዲቆዩ ተደርገዋል፡፡

በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ እንዳስታወቀው ከሚመለከታቸው የሀገሪቱ የስራ ኃላፊዎች ጋር በመነጋገር ዜጎቹ እንዲፈቱ ተደርጓል፡፡

ከቤተሰቦቻቸው ጋር ታስረው የነበሩ ህፃናትም የህክምና ክትትል እና ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ መቻሉንም አሳውቋል።

The post የሳዑዲ ዓረቢያን የመኖሪያ ፈቃድ ተላልፈዋል በሚል ላለፉት ሳምንታት በሪያድ ፖሊስ ጣቢያዎች የቆዩ 82 ዜጎች ከእስር ተፈቱ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply