የሳፋሪኮም መምጣት ተኝቶ የነበረውን ኢትዮ ቴሌኮምን ቀስቅሷል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ የሳፋሪኮም ወደ ኢትዮጵያ መግባት ኢትዮ ቴሌኮምን ከተኛበት ቀስቅሶታል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ይህንን በባንኩም ዘርፍ መድገም እንፈልጋለን ነዉ ያሉት፡፡

ከ47 ሚሊየን በላይ የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚዎች እንዳሉ የገለጹት ጠቅላይ ሚነስትሩ አሁንም ከዚህ በላይ መስራት እንደሚቻል አንስተዋል፡፡

ለዚህም በኢትዮ ቴሌኮም እንዳደረግነው ሁሉ በባንኩ ዘርፍ ተሰማርተው የሚገኙ የውጭ ድርጅቶችን ወደ ሃገር ውስጥ ማስገባት አንዱ መፍትሄ ነው ብለዋል፡፡

በሊዲያ ደሳለኝ

ሰኔ 27 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply