የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሴቶች በህብረት እና በአንድነት ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባ ተገለፀ

የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሴቶች በህብረት እና በአንድነት ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሴቶች በህብረት እና በአንድነት ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባ ገለፁ ።
የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ማህበር 7ኛ መደበኛ ጉባኤ 2ኛ ዓመት 1ኛ የምክር ቤት ጉባኤ አካሂዷል ።
በጉባዔው ምክትል ከንቲባ እና የማህበሩ የቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እንደገለፁት÷ ሃገሪቱን ለመበታተን እና ሰላሟን ለማደፍረስ የተቃጣውን እኩይ ሴራ በማክሸፍ ረገድ ሴት የመከላከያ ሰራዊት የፈፀሙት ጀብድ የሚያኮራ መሆኑን ገልጸዋል ።
የከተማዋ ሴቶች መብታቸውን እና ሁለንተናዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ የሚያደናቅፉ ችግሮችን በመታገል ሴቶች በህብረት እና በአንድነት ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባም መናገራቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሴቶች በህብረት እና በአንድነት ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባ ተገለፀ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply