የሴቶችን ቀን ከማክበር ባሻገር የሚወጡ ህጎችንም እንከታተል—ኤድስ ኸልዝ ኬር ፍውንዴሽን

ሀገርን ማበልፀግ ከተፈለገ የሀገሪቱ 50 በመቶ የሚሆኑት ሴቶችን ማብቃት ግድ እንደሚል የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ተናገሩ።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ኢትዮጵያ ከ50 በመቶ በላይ ሴቶች ያሉባት ሀገር በመሆኗ ኢትዮጵያ ሰላምና ፀጥታዋ እንዲጠበቅ እንዲሁም በቴክኖሎጂ እንድታድግ ከተፈለገ ለሀገራችን ስንል ሴቶችን ማብቃት ግድ ይለናል ብለዋል።

የዘንድሮ አለም አቀፍ የሴቶች ቀን በዓለም ለ113ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ48ኛ ጊዜ “ሴቶችን እናብቃ ልማትና ሠላምን እናረጋግጥ” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተከብሯል።

የኤድስ ኸልዝ ኬር ፍውንዴሽን (AHF) ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር ዶከተር መንግስቱ ገ/ሚካኤል ፤የዘንድሮው ዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀን ሲከበር ፆታን መሰረት አድርገው የሚሰነዘሩ ትንኮሳዎችን ማስቀረትና የሚወጡ ህጎች ላይም በአግባቡ ክትትል ማድረግ እንደሚገባ ጠቅሰዋል።

በዚህም ክብርበዓል የአዲስ አበባ ዩኒቨረሲቲ ፣ጤና ሚኒሰቴርና በኤችአይቪ ላይ የሚሰራው AHF ኢትዮጵያ በጋራ በመሆን ለ6ሺህ አቅመ ደካማ የአዲስ አበባ ዩኒቨረሲቲ ተማሪዎች፣እንዲሁም ለ9ሺህ 6መቶ 40 ለሚሆኑ ለአካል ጉዳተኞች ማህበር የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ሞዴስ ድጋፍ አድርጓል።

በሴቶች ላይ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ የሰብአዊ መብት ግዴታ እና ሁሉን አቀፍ የማህበረሰብ እድገት መሰረት መሆኑን ተረድተን ለሴቶች የሚደረገውን ድጋፍ አጠናክረን መቀጠል አለብንም ብለዋል፡፡

በልዑል ወልዴ

የካቲት 30 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply