የሴቶች ቀንን በማስመልከት በሶስት የሴቶች ትውልድ መሪዎች መካካል ያለውን ግንኙነት የሚያጠናክር የፓናል ውይይት ተካሄደ

የሴቶች ቀንን በማስመልከት በሶስት የሴቶች ትውልድ መሪዎች መካካል ያለውን ግንኙነት የሚያጠናክር የፓናል ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የዘንድሮ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን /ማርች 8/ በማስመልከት በይነ ትውልድ በሶስት የሴቶች ትውልድ መሪዎች መካካል ያለዉን ግንኙነት የሚያጠነክር የፓናል የዉይይት መድረክ ተካሂዷል፡፡

የዘንድሮ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን በማስመልከት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በይነ ትውልድ በሶስት የሴቶች ትውልድ መሪዎች መካካል ያለዉን ግንኙነት የሚያጠነክር የፓናል የዉይይት መድረክ አካሂዷል፡፡

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የሴቶች፤ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ሚኒስትር ወይዘሮ ፊልሰን አብዱላሂለተሳታፊዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ካስተላለፉ በኋላ የዘንድሮ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ከወትሮ ለየት ባለ መልኩ በተለያዩ የንቅናቄና ግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሞች ወሩን ሙሉ በአራት ዓበይት መረሃ ግብሮች የሚከበር መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የፓናል ዉይይቱም በሶስት የሴቶች ትውልድ መሪዎች መካካል ያለዉን ግንኙነት የሚያጠርናክርና የንቅናቄ መረሃ ግብሩ አካል መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በፓናል ውይይቱ ላይ አንጋፋዎቹን ሴት መሪዎች በመወከል ከተሳተፉ መሪዎች መካከል የመጀመሪያዋ የሴቶች ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታደለች ኀ/ሚካኤል፣ በኢትዮጵያ በስርዓተ-ፆታ እኩልነትና በሴቶች መብት ላይ ስልጠና በመስጠት ፋናወጊ የሆኑት ወ/ሮ ዘውዴ አበጋዝ ፤ የአዲስ ሕይወት ዓይነ-ስውራን ማህበር ዳይሬክተር ወይዘሮ አፄ-ባዩሽ አበበ፣ በ1969 የመጀመሪያዋ ሴት የኢህአፓ የወጣት ክንፍ መሪ የነበሩት ወ/ሮ ቆንጂት ብረሃነ ይገኙበታል፡፡

የመካከለኛውን ዘመን ሴት መሪዎች በመወከል የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስትር ወይዘሮ ፊልሰን አብዱላሂ እና የሴታዊት ንቅናቄ መስራች ዶክተር ስህን ተፈራ፤ አንዲሁም ወጣት ሴት መሪዎችን በመወከል ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ክፍል የሦስተኛ ዓመት ተማሪና የዬሎ ሙቭመንት አባል በፀሎት ከፈለኝ እንዲሁም ከጅግጅጋ ዩኒቨርሱቲ የማኔጅመንትና የነርሲንግ የሁለተኛ ዓመት ተማሪ ምህረት ዋለልኝ መሳተፋቸውን ከሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post የሴቶች ቀንን በማስመልከት በሶስት የሴቶች ትውልድ መሪዎች መካካል ያለውን ግንኙነት የሚያጠናክር የፓናል ውይይት ተካሄደ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply