የሴኔጋሉ ተቃዋሚ መሪ በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች መታሰራቸው ተሰምቷል፡፡

ሬውተርስ የዜና ምንጭ የዓይን እማኞችን ጠቅሶ ባሰራጨው ዘገባው የሴኔጋል ተቃዋሚ ፓርቲ መሪው ኡስማን ሶንቆ ታስረዋል፡፡በዋና ከተማዋ ዳካር በመቶ የሚቆጠሩ የኡስማን ሶንቆ ደጋፊዎች ከፖሊስ ጋር መጋጨታቸውን ተከትሎ በተወሰደ እርምጃ ነው ሶንቆ ዘብጥያ መጣላቸው የተሰማው፡፡

አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ባሰራጨው ዘገባው ዳግሞ የ46 ዓመቱ የሴኔጋሉ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ኡስማን ሶንቆ በህዝብ ዘንድ ተቀባይነታቸው በመጨመሩ ባለፈው ወር በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተጠርጥረው በመንግስት እንዲታሰሩ መደረጉን አስታውሷል፡፡ሶንቆ በፍርድ ቤት ተገኝተው ምላሽ እንዲሰጡ ሲወሰዱ በፖሊስ ድብደባ እንደተፈፀመባቸውና የጉዳዩን አሳሳቢነት ጠበቃቸው መግለፃቸውን የዘገበው አል አፍሪካ ነው፡፡

ቀን 26/06/2013

አሐዱ ራድዮ 94.3

Source: Link to the Post

Leave a Reply