የሴኔጋል ተቃዋሚዎች የምርጫ ዉጤት እንዲታገድ ጠየቁ::የሴኔጋል ተቃዋሚዎች በሀገሪቱ የተካሄደውን የህግ አውጪ ምክር ቤት ምርጫ ተከትሎ ውጤቱ ከመታተሙ አስቀድሞ ግምገማ ይደረግበት ሲሉ ጠይቀዋ…

የሴኔጋል ተቃዋሚዎች የምርጫ ዉጤት እንዲታገድ ጠየቁ::

የሴኔጋል ተቃዋሚዎች በሀገሪቱ የተካሄደውን የህግ አውጪ ምክር ቤት ምርጫ ተከትሎ ውጤቱ ከመታተሙ አስቀድሞ ግምገማ ይደረግበት ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

በጥምር ፕሬዝዳንቱ ቁጥጥር ስር የሚገኘዉን 165 ወንበር ለማሻሻል ከተካሄደዉ ድምጽ በኋላ ተቃዋሚዎች ድል እያደረጉ እንደሚገኙ እየተገለጸ ነዉ፡፡

ዴቲሂ ፎል የተባለ የተቃዋሚ ፓርቲ አባል እንደተናገሩት፣ የብሄራዊ የምርጫ ኮሚሽኑ ዛሬ ይፋ ይደረጋል ተብሎ የነበረው የምርጫ ዉጤት እንዳይታተም ጠይቀዋል፡፡

እንዲሁም ኮሚሽኑ የምርጫ ዉጤቱን ከሴኔጋል ህዝብ ጋር ተቀባይነት የሌላቸዉን ህገ ወጥ ድርጊቶች ይገምግም በማለት ጋዝጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ሌላኛዉ የተቃዋሚ ፓርቲ አባል ኦስማን ሶንኮ አንድ ሰዉ ይህንን ያህል ድምጽ ሊያገኝ አይችልም በማለት ይህንን ድምጽ ለመዉረስ የተደረገ ሙከራ ባለመቀበል ለፕሬዝዳንት ማኪ ሳል አቤት እላለሁ ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ተቃዋሚዎቹ ምርጫዉ የተከፋፈለዉ መንግስት ለሶስተኛ የስልጣን ዘመን ሊኖረዉ የሚችለዉን ስልጣን ይገታል የሚል ተስፋ እንደነበራቸዉ ተሰምቷል፡፡

እ.ኤ.አ በ 2024 ከሚደረገዉ የመጨረሻ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በፊት በጥር ወር አካባቢ ተቃዋሚዎች በዋና ከተማዋ ዳካር እና በሌሎች ከተማዎች ማሸነፍ ለማ ሳል ፈተና ሆኖ ቆይቶ ነበር፡፡

በቤዛዊት አራጌ
ሐምሌ 28 ቀን 2014 ዓ.ም

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

ዌብሳይት https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply