የሴካፋ ካጋሜ ካፕ ውድድር ያካሄዳል ! በሴካፋ አባል ሀገራት የውድድር አሸናፊ ክለቦች መካከል የሚደረገው የሴካፋ ካጋሜ ካፕ ውድድር በቀጣይ ሐምሌ ወር በታንዛኒያ አዘጋጅነት ሊካሄድ መሆኑ ይ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/NWILOR7EDmBNBpdkTSq20Zb5G9FFysBMIjPE_3k0XptLbqQosvrX8KfkzPJMV1kcdgBrf6a1gk8xlEHzbNH763sg6dVcVJwUmPZdTuZAXs4MlZ8TI-3zWIVQ4voHElbraefSmnRisNysRav0n-EJq6P8cXAWEj1R3pQTBRdAIXqiwng9hdrdQ3HJNbXnbiAs-QYLAlxJHHuQnLIvAEZWhO9QPty5jyIAE8i4CasUcpYDg15GV8of_XPHLqX3YeWLdyQ3mGcRC76pzWm0ftjIR2EV5iUAC-kn4ZglvRKuFmFAN5T9D8G6mYCOwKE35KflJh2iI_p5batsFZsqOWJHEg.jpg

የሴካፋ ካጋሜ ካፕ ውድድር ያካሄዳል !

በሴካፋ አባል ሀገራት የውድድር አሸናፊ ክለቦች መካከል የሚደረገው የሴካፋ ካጋሜ ካፕ ውድድር በቀጣይ ሐምሌ ወር በታንዛኒያ አዘጋጅነት ሊካሄድ መሆኑ ይፋ ተደርጓል።

በውድድሩ ሀገራችን ኢትዮጵያን ጨምሮ የአስራ ሁለት የሴካፋ አባል ሀገራት አሸናፊ ክለቦች እንዲሁም አራት ተጋባዥ ክለቦች እንደሚሳተፉ ተገልጿል።

ይህም ማለት የዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አሸናፊ ክለብ ኢትዮጵያን ወክሎ በውድድሩ ተሳታፊ የሚሆን ይሆናል።

ላለፉት አመታት ተቋርጦ የነበረው ውድድሩ በታንዛንያ አዘጋጅነት ከሐምሌ 13 /2016 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 28/2016 ዓ.ም እንደሚካሄድ ይፋ ሆኗል።

የሴካፋ የክለቦች ካጋሜ ካፕ ውድድር ለመጨረሻ ጊዜ የተደረገው ከሶስት አመት በፊት 2021 ታንዛኒያ ዳሬ ሰላም ከተማ እንደነበር ይታወሳል።

ግንቦት 6 ቀን 2016ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply