የስልጣን ሽግግር እስከሚደረግ ድረስ የጸጥታ ሁኔታው በተማከለ ኮማንድ ዕዝ ሊመራ ይገባል  ሲል የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም አስታወቀ አሻራ ሚዲያ መጋቢት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ባህርዳር የኢት…

የስልጣን ሽግግር እስከሚደረግ ድረስ የጸጥታ ሁኔታው በተማከለ ኮማንድ ዕዝ ሊመራ ይገባል ሲል የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም አስታወቀ አሻራ ሚዲያ መጋቢት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ባህርዳር የኢት…

የስልጣን ሽግግር እስከሚደረግ ድረስ የጸጥታ ሁኔታው በተማከለ ኮማንድ ዕዝ ሊመራ ይገባል ሲል የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም አስታወቀ አሻራ ሚዲያ መጋቢት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ባህርዳር የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ባወጣው መግለጫ በጊዚያዊነት 6ኛው ብሄራዊ እና ክልላዊ ምርጫ ተከናውኖ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እስከሚያደርግ ድረስ የሀገሪቷ የጸጥታ ተግባር በተማከለ ኮማንድ ዕዝ ሊመራ ይገባል ብሏል። የተለያየ የኅብረተሰብ ክፍል ተሰባጥሮ በሚኖርበት ትላልቅ ከተሞች ላይ ከሁሉም ክልሎች በተውጣጣ የልዩ ፖሊስ ኃይል የዜጎችን ሰላም እና ጸጥታ እንዲጠበቅ ምክረ-ሃሳባችንን እናቀርባለን ያለው ተቋሙ መንግስት የሰላም ሚኒስቴርን አደረጃጀት ሊከልስ ይገባል ሲል ገልጿል። በዚህ መሰረት ላለፉት ዓመታት የነበረዉ አሁንም ተባብሶ የቀጠለዉ አገራዊ ችግር በተለይም የንጹሃን ዜጎች ሞትና መፈናቀል በአጠቃላይ የህግ የበላይነት አለመከበር በእጅጉ ያሳስበናል ሲል የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ተናግሯል ብሏል ብሎ የዘገበው የአዲስ ዘይቤ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply