የስም ማጥፋት ዘመቻ ደርሶብኛል ያለው ኦክሎክ ሞተርስ 230 ተሽከርካሪዎች ለደንበኞቹ አቀረበ።ኦክሎክ ሞተርስ ከ2012 አመት ጀምሮ የተለያየ ሞዴል ያላቸው ተገጣጣሚ ተሽከርካሪዎች ከውጭ ሀገራ…

የስም ማጥፋት ዘመቻ ደርሶብኛል ያለው ኦክሎክ ሞተርስ 230 ተሽከርካሪዎች ለደንበኞቹ አቀረበ።

ኦክሎክ ሞተርስ ከ2012 አመት ጀምሮ የተለያየ ሞዴል ያላቸው ተገጣጣሚ ተሽከርካሪዎች ከውጭ ሀገራት በማስመጣት በፋብሪካው በመገጣጠም ለደንበኞቹ በማቅረብ ላይ የሚገኝ ድርጅት ነው።

ድርጅቱ ባሁኑ ሰአት መንግስት የቀረጥ ነጻ ከሰጣቸው ከ60 ማህበራት ጋር የሽያጭ ውል በመግባት ሙሉ በሙሉ ተበታትነው ሀገር ውስጥ ገብተው የሚገጣጠሙ ተሽከርካሪዎችን እየገጣጠመ ለደንበኞቹ እያቀረበ እንደሆነ ገልጿል።

ከድርጅቱ መኪና ለመውሰድ የተመዘገቡ ደንበኞች በቅድምያ 36በመቶ በመክፈል የተቀረው ደግሞ ከአበዳሪ ባንኮች ጋር ውል በማስገባት እንደሚከፍሉ ነው የተገለጸው።

ኦክሎክ ከዚህ በፊት ከቀረጥ ነጻ ፍቃድ ላላቸው ማህበራት ከ200 በላይ መኪኖችን ማስረከቡንም ገልጿል።

በቀጣይ ከ200 በላይ ለሚሆኑ አባላት ተሽከርካሪዎች ለማስተላለፍ እንዲቻለው ማህበራቱ ከአበዳሪ ተቋማት የመተማመኛ ደብዳቤ አምጥተው ተሽከርካሪዎቹን መረከብ ይችላሉ ተብሏል።

አሁን ከቀረጥ ነጻ ፍቃድ ላላቸው ስምንት ማህበራት ውስጥ ለሚገኙ አባላት እንደየመኪና ምርጫቸው መኪናዎቹን እያስተላለፈ እንደሚገኘ አስታውቋል።

ኦክሎክ ሞተርስ ከሰሞኑ ከደንበኞቹ ለተነሳበት ቅሬታም መልስ የሰጠ ሲሆን ሁሉም በህግ አግባብ ተከናውኗል ሲል ገልጿል።

35 ቅድሚያ ክፍያ ከፍለው ገዡዎች ቢዋዋሉም ቀሪውን 65 በመቶ ለመክፈል ከአበዳሪ ተቋም የመተማመኛ ደብዳቤ ካላመጡ መኪና ልናስረክብ አንችልም ብሏል።

አሁንም እጃችን ላይ ወደ 200 መኪናዎች አሉን ለማስረከብ ዝግጁ ነን።

ከእኛ ጋር ውል የገቡ ማህበራት አባላት የብድር መተማመኛ ከአበዳሪ ተቋም ካመጡ መኪናውን መውሰድ ይችላሉ።

1ሺህ 500 ተመዝጋቢዎች አሉን ከዚህ ውስጥ 400 ገደማው ቅድሚያ የሚጠበቅባቸውን 35 ፐርሰንት የከፈሉ ናቸው።

62 ማህበራት ከእኛ ጋር እየሰሩ ነው 22ቱ ማህበራት. ወደ ሚዲያ ሄደዋል።

ከውል ውጭ ያደረግነው ነገር የለም ብሏል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

መጋቢት 27 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply