You are currently viewing የስሪላንካ ፕሬዝዳንት ሀገሪቱን ለቀው ተሰደዱ አምሰተርዳም ፥ ሀምሌ 6 2014 ዓም አሻራ ሚዲያ ፕሬዝዳንቱ የሚመሯትን ሀገር ጥለው የተሰደዱት በተነሳባቸው ህዝባዊ ተቃውሞ ምክንያት ነው የስሪ…

የስሪላንካ ፕሬዝዳንት ሀገሪቱን ለቀው ተሰደዱ አምሰተርዳም ፥ ሀምሌ 6 2014 ዓም አሻራ ሚዲያ ፕሬዝዳንቱ የሚመሯትን ሀገር ጥለው የተሰደዱት በተነሳባቸው ህዝባዊ ተቃውሞ ምክንያት ነው የስሪ…

የስሪላንካ ፕሬዝዳንት ሀገሪቱን ለቀው ተሰደዱ አምሰተርዳም ፥ ሀምሌ 6 2014 ዓም አሻራ ሚዲያ ፕሬዝዳንቱ የሚመሯትን ሀገር ጥለው የተሰደዱት በተነሳባቸው ህዝባዊ ተቃውሞ ምክንያት ነው የስሪላንካ ፕሬዝዳንት ሀገሪቱን ለቀው ወደ ማልዴቪስ ተሰድደዋል። በእስያዋ ስሪላንካ በተከሰተው የኢኮኖሚ ቀውስ ምክንያት ላለፉት ሳምንታት ህዝባዊ ተቃውሞ በመላ ሀገሪቱ ሲካሄድ ቆይቷል፡፡ ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ፕሬዝዳንት ጎታብያ ራጃፓክሳ ስልጣን እንዲለቁ ሲጠይቁ የቆዩ ሲሆን በመጨረሻም ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ፕሬዝዳንቱ ስልጣን ለመልቀቅ ተገደዋል፡፡ ተቃዋሚዎች ባሳለፍነው ቅዳሜ በሀገሪቱ መዲና በሆነችው ኮሎምቦ ከተማ የሚገኘውን ቤተመንግስት የተቆጣጠሩ ሲሆን የብዙዎችን ትኩረት የሳበ ድርጊቶችን ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ ተቃውሞ የበረታባቸው የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ራጃፓክሳም ወደ ጎረቤት ሀገር ማልዴቪስ እንደተሰደዱ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ የማልዴቪስ መንግስት እንደገለጹት ስልጣን የለቀቁት የስሪላንካ ፕሬዝዳንት ወደ ሀገራቸው እንደመጡ ገልጸው ወደ ሌላ ሀገር የማቅናት እቅድ እንዳላቸውም ተናግረዋል፡፡ የቀድሞው ፕሬዝዳንት በተነሳባቸው ተቃውሞ ቤተ መንግስታቸውን ለቀው ባልታወቀ ስፍራ ተደብቀው የቆዩ ቢሆንም ከሰዓታት በፊት ከሁለት ጠባቂዎቻቸው ጋር ወደ ጎረቤት ሀገር መጓዛቸው ተገልጿል፡፡ ፕሬዝዳንቱ የደቡብ እስያዋ ስሪላንካን ላለፉት 20 ዓመታት የመሩ ቢሆንም በአሳዛኝ ሁኔታ በህዝባዊ ተቃውሞ ተገደው ከስልጣን ሊለቁ ችለዋል፡፡ 22 ሚሊዮን ህዝብ ያላት ስሪላንካ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ችግር የገጠማት ሲሆን ነዳጅን ጨምሮ ከውጪ የሚገቡ ምርቶች ከፍተኛ እጥረት በማጋጠሙ ህዝቡ ወደ አደባባይ ከወጣ ወራትን አስቆጥሯል፡፡ ሀገሪቱ የውጭ ምንዛሬ እጥረቱ ከእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ነጻ ከወጣችበት ከፈረንጆቹ 1948 ጀምሮ የነበረ ሲሆን በዚህ ዓመት ግን ችግሩን ለመቋቋም መቸገሯ ነው የተገለጸው፡፡ ለዜጎቿ ምግብ፣ ነዳጅ እና መድሃኒቶችን መሰል መሰረታዊ ፍላጎቶችን ለማቅረብ ተቸግራለችም፡፡ ለአንድ ዓመት 6 ነጥብ 9 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ መጠባበቂያ በጀት የሚያስፈልጋት ቢሆንም አሁን ላይ የአገሪቱ መጠባበቂያ የውጭ ምንዛሬ መጠን እጅግ መሟጠጡ ተገልጿል፡፡ ©አል አይን አማርኛ

Source: Link to the Post

Leave a Reply