የስርዓተ ፆታን እኩልነት በተመለከተ የመገናኛ ብዙሃን የሚጠበቅባቸዉን ያህል እየሰሩ አይደለም ተባለ፡፡በኢትዮጵያ የሚገኙ የመገናኛ ብዙሃን የሴቶችን የመስራት እና ተፅእኖ የመፍጠር አቅማቸውን…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/obnIWHQ6KcFYsaTsCagpRanQRfpWR6NZ9dQcfXY-Eg78udwzXQvoZALMZ_d-yD8W8lWsMV1kGhjhP7TB4th1_ZVDgPGG3Ze1DoCoWlYeCDTXXugMW0w3YBCVKzQrsK5gWj4xCxcD2MKlLz-DmaUcvDu0_1fZXjoDJNsJeM0RVmikb4Y7lVZEULxaSWfOMaGLO3_L9KugTQn_nCE1rhPQWvJXvQ2FHR-skacLBvgP-J08Moi5jUjznp-sLvhdWjUpKXGKSc5MRcjsOxVYs5WaS20R05bo8WMERzkU3oqKttxOJcWSkL1JnWsKpHQ6zTg2wPJ43G7sH7kP7XbhXuAA0Q.jpg

የስርዓተ ፆታን እኩልነት በተመለከተ የመገናኛ ብዙሃን የሚጠበቅባቸዉን ያህል እየሰሩ አይደለም ተባለ፡፡

በኢትዮጵያ የሚገኙ የመገናኛ ብዙሃን የሴቶችን የመስራት እና ተፅእኖ የመፍጠር አቅማቸውን ከማጎልበት አንጻር የሚጫወቱት ሚና አናሳ መሆኑን የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ከአክት ኦን ኤድ ጋር በመተባበር በጥናት አረጋግጫለው ብሏል።

የማህበረሰብ መገምቢያ ዋናው መሳሪያ የሆነው መረጃ የሚተላለፍባቸው መገናኛ ብዙሀን በዘመናዊ መልክ እድገት የጀመረው፣በ1895 ዓ.ም ቢሆንም ካሉት ጋዜጠኞች 30 በመቶ ብቻ የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸው በስርአተ ፆታ እኩልነት ዙሪያ ያለው ፍትሃዊነት አናሳ መሆኑን እንደሚያሳይ የቢቢሲ ጥናታዊ ሪፖርት ያሳያል፡፡

ሴቶች ግማሽ የማህበረሰቡ አካል እንደመሆናቸው ከማስተማር ጀምሮ በከፍተኛ በአመራር ደረጃ እስከመሾም ብሎም የውሳኔ አካል ለማድረግ መንግስት፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና መገናኛ ብዙሀን በጥልቀት ሊሰሩ እንደሚገባም ተነግሯል።

በቤዛዊት አራጌ
ጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን
ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply