የስታር ሆቴሉ ስብሰባ (ታህሳስ16፣2013ዓ.ም ባህርዳር)  የንፅሃን  ቄራ በሆነው መተከል ዞን ያለውን ሁኔታ በተመለከተ ዛሬ የጦር ጀኔራሎች እና እነ አሻድሌ ሀሰን ግልገል በለስ  በዝግ እ…

የስታር ሆቴሉ ስብሰባ (ታህሳስ16፣2013ዓ.ም ባህርዳር) የንፅሃን ቄራ በሆነው መተከል ዞን ያለውን ሁኔታ በተመለከተ ዛሬ የጦር ጀኔራሎች እና እነ አሻድሌ ሀሰን ግልገል በለስ በዝግ እ…

የስታር ሆቴሉ ስብሰባ (ታህሳስ16፣2013ዓ.ም ባህርዳር) የንፅሃን ቄራ በሆነው መተከል ዞን ያለውን ሁኔታ በተመለከተ ዛሬ የጦር ጀኔራሎች እና እነ አሻድሌ ሀሰን ግልገል በለስ በዝግ እየመከሩ ነው፡፡ በምክክሩ እነ ጀኔራል ብርሃኑ ጁላን ጨምሮ የአሻድሌ ካድሬዎች ተገኝተዋል፡፡ የመተከል ዞን አመራሮች በብዛት ወደ ጫካ ስለገቡ ስብሰባውን አልታደሙም፡፡ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪም ከስብሰባው አልገባም፡፡ ይህ ውይይት ምንም አይነት መፍትሄ ሊያመጣ እንደማይችል ግን የመተከልን የፖለቲካ ሁኔታ እና የሀገሪቱን ቁመና የተመለከቱ ሁሉ እየተናገሩ ነው፡፡ ለዚህም የሚከተለውን ሀሳብ በአስረጅነት ያነሳሉ፡፡ 1)ብልፅግና ሀገራዊ ዓላማ ስለሌለው ግጭቶችን የሚያቆምበት የመውጫ መንገድ የለውም፡፡ 2) ወታደሩ በሱዳን ፣በትግራይ እና በልዮ ልዮ የሀገሪቱ ክፍሎች ህ…ግ እያስከበረ በመሆኑ 3) ወታደሩ ለመተከል መልካዓምድራዊ አቀማመጥ እንግዳ መሆኑ እና ታጣቂዎች በመልካዓምድሩ ተጠቃሚ መሆናቸው 4) የቢሻንጉል ጉምዝ አመራሮች ቀን ቀን መንግስት ማታ ማታ ሽፍታ መሆናቸው 5) የኦሮሚያ ብልፅግና ህወኃትን ለመሆን ያለ ይሉኝታ መንቀሳቀሱ 6) የአማራ ብልፅግና ፖለቲካዊ ድንቁርና መኖሩ ከማዕከላዊ መንግስቱ እያለ አለመኖሩ ናቸው፡፡ 7) ብልፅግና ህግ የሚያስከብረው ለለበጣ እና ለወንበሩ እንጂ ንፁሃንን ለማዳን አይደለም፡፡ ይህ በመሆኑም የስታር ሆቴሉ ስብሰባ ፍሬ ቢስ ሊሆን ይችላል እየተባለ ነው፡፡ በመተከል ሙሉ በሙሉ የመንግሥት መስሪያቤት ዝግ መሆኑን አሻራ ሰምቷል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply