የስንዴ ዱቄት የጫነ በማስመሰል ወደ አዲስ አበባ ሊገባ የነበረ ከ16 ሚሊዮን በላይ ብር የሚገመት የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ።ከ16 ሚሊዮን በላይ ዋጋ ያላቸው መድሀኒት እና  የልብስ…

የስንዴ ዱቄት የጫነ በማስመሰል ወደ አዲስ አበባ ሊገባ የነበረ ከ16 ሚሊዮን በላይ ብር የሚገመት የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ።

ከ16 ሚሊዮን በላይ ዋጋ ያላቸው መድሀኒት እና የልብስ ቦንዳ በህገወጥ መንገድ ወደ አዲስ አበባ ሲገባ በቱሉ ዲምቱ መቆጣጠርያ ጣብያ መያዛቸውን ሰምተናል፡፡

በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉሙሩክ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የቱሉ ዲምቱ መቆጣጠርያ ጣብያ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው ፍተሻ ሲደረግበት ለማምለጥ የሞከረው የጭነት መኪና በኮንትሮባንድ ቁጥጥር ክትትል 2ኛ ዲቪዥን 4ኛ ሻለቃ 4ኛ ሀይል የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በወሰደው እርምጃ ለማስቆም መቻሉን ኤትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል።

በፍተሻው ወቅት መኪናው እህል የጫነ በማስመሠል እና ሰላማዊ ሆኖ ለመንቀሳቀስ መሞከሩ ተነግሯል።

ይሁን እንጂ በተደረገው ጥብቅ ፍተሻ አሽከርካሪው መኪናውን ለማንቀሳቀስ የሞከረ ቢሆንም በተወሰደ የሀይል እርምጃ መኪናው በጥይት ተመቶ የቆመ መሆኑ ተነግሯል።

በዚህ እርምጃ በሰው ላይም ምንም አይነት ጉዳት አልደረሰም።

በህገ-ወጥ መንገድ ሊገባ የነበረው የተለያዩ መድሀኒቶቹ እና የልብስ ቦንዳ ወደ አዲስ አበባ ከመግባቱ አስቀድሞ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉሙሩክ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የቱሉ ዲምቱ መቆጣጠርያ ጣብያ ኃላፊ አቶ ዋርዮ ጉዮ ለጣቢያችን አሳውቀዋል።

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የወረዳ 2 አስተዳደር ሰላም እና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ ኢንስፔክተር አይናለም ግርማ እንደገለፁት በቁጥጥሩ የተያዘው የተለያዩ መድሀኒቶች በህብረተሰቡ ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርሱ መሆናቸው ገልጸዋል።

ህገወጥ አልባሳቱም ቢሆን በኢኮኖሚው ላይ ያልተገባ ተፅዕኖ ሊያመጣ እንደሚችል ከሀላፊዎቹ ሰምተናል።

በያይኔአበባ ሻምበል
የካቲት 16 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply