የስፔይን ወሰን ጠባቂዎች በከናሪያ ደሴቶች 23 ፍልሰተኞች አተረፉ

https://gdb.voanews.com/03990000-0aff-0242-04a1-08daab97c6e6_w800_h450.jpg

የስፔይን ወሰን ጠባቂዎች በአትላንቲክ ውቂያኖስ ላይ ያገኟቸውን 23 ፍልሰተኞች ትናንት ሰኞ ግራን ከናሪያ ደሴት ወደምትገኘው አርጊኔጊን ወደብ በጀልባ ማጓጓዛቸውን ቀይ መስቀል አስታወቀ፡፡ 

ከአደጋ የተረፉት ፍልሰተኞች ሁሉም አፍሪካዊያን ወንዶች ሲሆኑ ከደሴቲቱ በስተደቡብ 40 ማይል ርቀት ላይ የተገኙ መሆኑን ወሰን ጠባቂዎቹ ተናግረዋል፡፡

በየዓመቱ በሺዎቹ የሚቆጠሩ ሰዎች ከሰሜን አፍሪካ የተቃና ኑሮ ፍለጋ ወደ አውሮፓ እንደሚጓዙ የተገለጸ ሲሆን እኤአ በ2020 23ሺ 271 የሚሆኑ ፍልሰተኞች በከናሪያ ወደብ በኩል በጀልባ ባህሩን አቋርጠው ስፔን መግባታቸው ታውቋል፡፡

ባለፈው በ2021 ደግሞ 22ሺ316 ሰዎች በተመሳሳይ መንገድ መሻገር መቻላቸውን ከስፔይን አገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው አሃዝ ገልጿል፡፡

ባላፈው ዓመት ወደ ስፔይን አቋርጠው መግባት የሞከሩ 4ሺ 400 የሚሆኑ ሰዎች ከባህሩ ተሰውረው መቅረታቸውን ሁኔታውን የሚከታተለው ቡድን አስታውቋል፡፡

ባላፈው ሳምንት ከአፍሪካ ወደ አውሮፓ ይጓዙ የነበሩ 33 ስደተኞች ከ9 ቀናት ጉዞ በኋላ በነበሩበት ጀልባ ላይ ሞተው መገኘታቸውን እና አንድ ፍልሰተኛ ብቻ በህይወት እንደተገኘ መዘገቡ ይታወሳል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply