የስፖርት አወራራጅ ወይም ቤቲንግ ቤቶች ቢዘጉም በኦላይን እየሰሩ መሆናቸው ተገለጸ፡፡

የስፖርት አወራራጅ ድርጅቶች በአካል ቢዘጉም አሁንም ላይ በኦላይን አገልግሎት እየሰጡ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

ከዚህ በፊት ከብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ፍቃድ ወስደው ሲሰሩ የነበሩ ግን ደግሞ ፍቃዳቸው የተሰረዘባቸው ድርጅቶች ሳይቀሩ በኦላይን አማካኝነት ስራቸውን እየሰሩ እንደሚገኙ ኢትዮ ኤፍ ኤም ከብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ሰምቷል፡፡

የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር የኮሚኒኬሽን ዳሬክተር አቶ ቴወድሮስ ንዋይ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ውርርድ ቤቶቹ ላይ እርምጃ ቢወሰድም በኦላይን እየሰሩ ናቸው ብለዋል፡፡

እነዚህ በኦላይን የስፖርት ውርርድ የሚሰሩ ድርጅቶች መቆጣጠር ያልተቻለው ቴክኖሎጂውን እና የሚያጫውቱበት ሲስተም የሚያቀርቡላቸው ተቋማት መቆጣጠር ባለመቻሉ ነው ብለዋል፡፡

የአወራራጅ ድርጅቶች ሲስተም የሚያቀርቡት እስካሁን ድረስ እነማን እንደሆኑ አይታወቅም ብለዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም በኦላይን ውርርድ ይሰራሉ የተባሉት ድርጅቶች የትኞቹ እንደሆኑ ለማረጋገጥ ድረገጾችን የፈተሸ ሲሆን እንደተባለው ድርጅቶቹ የተለያዩ አመራጭ መንገዶችን በመጠቀም ከበኦላይን እያወራራዱ እንደሚገኙ አረጋግጧል፡፡

አቶ ንዋይ እነዚህ ድርጅቶች መቆጣጠር የሚቻለው ቴሌ ኔትዎርክ ሲያቋርጥባች ብቻ ነው ብለዋል፡፡

ከሶስት ወራቶች በፊት በመዲናዋ በህገወጥ ተግባር ተሰማርተው የተገኙ 3 ሺህ 241 የስፖርት ውርርድ (ቤቲንግ) ቤቶች እንደታሸጉ ተነግሮ ነበር፡፡

እርምጃ የተወሰደባቸው ቤቶች ከተሰጣቸው የስራ ፍቃድ ውጭ ህገወጥ ተግባራት ሲፈጽሙና ንግድ ፈቃድ ሳይኖራቸው ሲሰሩ የተገኙ ናቸው ተብሎ ነበር፡፡

እነዚህ ቤቶች ከተሰጣቸው ፍቃድ ውጪ ሺሻ ማስጨስ፣ ጫት ማስቃም፣ አልኮል መጠጥ ሲሸጥባቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡

ተማሪዎች ትምህርታቸውን በማቋረጥ በዚህ ተግባር መሳተፋቸው፣ ብሄራዊ ሎቶሪ አስተዳደር ከ21 ዓመት በታች ያሉ ወጣቶች ውርርዱን እንዳይጫወቱ ካወጣው ደንብ በተጻራሪ ህጻናትን ጭምር ሲያጫወቱ ተደርሶባቸዋልም ነበር እርምጃ የተወሰደባቸው፡፡

በክትትልና በህብረተሰቡ ጥቆማ ህገወጥ ተግባር ሲፈጽሙ በተገኙት ላይ ቢሮው ከብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር፣ ከንግድ ቢሮ፣ ደንብ ማስከበር እና ከፖሊስ ጋር በመሆን እርምጃ መውሰዱ አይዘነጋም፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

መጋቢት 18 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply