የሶማሊላንድ ሕግ አውጪዎች ከኢትዮጵያ ጋር የተፈረመዉን ቀይ ባህርን በሊዝ የመጠቀም ስምምነት ዉድቅ አደረጉ፡፡ስምምነቱ ‹‹ህጋዊ ያልሆነ›› እንዲሁም የሶማሊላንድን ‹‹አንድነት የሚጎዳ›› ነዉ…

የሶማሊላንድ ሕግ አውጪዎች ከኢትዮጵያ ጋር የተፈረመዉን ቀይ ባህርን በሊዝ የመጠቀም ስምምነት ዉድቅ አደረጉ፡፡

ስምምነቱ ‹‹ህጋዊ ያልሆነ›› እንዲሁም የሶማሊላንድን ‹‹አንድነት የሚጎዳ›› ነዉ ሲሉ የፓርላማ አባላቱ ገልጸዋል፡፡

የሁለቱ የሶማሊላንድ ፓርላማ አባላት በጋራ ባወጡት መግለጫ ቀይ ባህርን ለመጠቀም የተገባዉ ስምምነት ህጋዊ ያልሆነ እንዲሁም የሶማሊላንድ ህዝቦችን አንድነት የሚጎዳ ነዉ ብለዋል፡፡

በይበልጥ ሀሳቡን የተቃወሙት ደግሞ ከአዉዳል እና ሳላል ክልሎች የመጡ ተወካዮች መሆናቸዉም ተገልጿል፡፡

ስምምነቱንም ሆነ ትግበራዉን አንቀበለዉም ፤ መንግስትም የተፈራረመዉን የመግባቢያ ስምምነት እንዲሰርዝ እንጠይቃለን ሲሉ በመግለጫዉ አክለዋል፡፡

ሶማሊያ ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር ያደረገችዉን ስምምነት ህጋዊ ያልሆነ እና ሉዓላዊነቴን የሚጥስ ነዉ ስትል ከዚህ በፊት መግለጿ ይታወሳል፡፡

ስምምነቱ ከተፈረመ በኋላም ሶማሊያ አምባሰደሯን ከኢትዮጵያ መጥራቷም የሚታወስ ነዉ፡፡

በፈረንጆቹ ጥር 1 ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር ካደረገችዉ ስምምነት በኋላ ከጎረቤት አገር ሶማሊያ ጋር ያለዉ ግንኙነት መካረሮች እየታዩበት ይገኛል ተብሏል፡፡

ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር ያደረገችዉ ስምምነት የትኛዉንም አካል ሆነ አገር የሚጎዳ አይደለም ስትል ገልጻለች፡፡

ኤርትራ በ1990ዎቹ መጀመሪያ ላይ ከኢትዮጵያ መገንጠሏን ተከትሎ ፤ ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባለቤትነቷን ማጣቷ ይታወቃል ሲል አናዶሉ ዘግቧል፡፡

እስከዳር ግርማ

የካቲት 07 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply