የሶማሊያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መባረር

የሶማሊያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መባረር ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ጋር እንደተያያዘ በተገመተ ምክንያት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯን አባረረች፡፡የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሃመድ ሁሴን ሮቤል ናቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን አህመድ ኢሴ አዋድን ከሥልጣን ያነሱት፡፡ተባራሪው ሚኒስትር አገራቸው በኢትዮጵያ በተለይም በትግራይ ክልል ባለው ወቅታዊ ጉዳይ አቋም አልያዘችም መግለጫም አላወጣችም ሲሉ በፃፉ ሰዓታት ልዩነት ከሥልጣናቸው ተነስተዋል፡፡የአገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለኢትዮጵያ አንድነት ድጋፍ እናደርጋለን ሲል መግለጫ ቢያወጣም፤ ሚኒስትሩ አገሪቱ ይፋዊ መግለጫ አላወጣችም ሲሉ በቲውተር ገፃቸው መፃፋቸው ለመባረራቸው ምክንያት መሆኑ ነው የተገመተው፡፡ሚኒስቴሩ ግን ሶማሊያ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) አስተዳደር ለሕገ መንግሥታዊ ማዕቀፎች እና የአገሪቱ ሉኣላዊነት መከበር ከሚወስዳቸው እርምጃዎች ጎን መሆኗን ያረጋግጣል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply