የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሸይኽ ማሕሙድ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ወደ አዲስ አበባ እንደሚገቡ ይጠበቃል። ፕሬዝደንቱ አዲስ አበባ የሚመጡት በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ነው።…

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሸይኽ ማሕሙድ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ወደ አዲስ አበባ እንደሚገቡ ይጠበቃል።

ፕሬዝደንቱ አዲስ አበባ የሚመጡት በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ነው።

አስቀድመው ስለ ጉዟቸው የተናገሩት ፕሬዝደንት ሐሰን፣ በስብሰባው ላይ ተገኝተን ሱማሊያ ጣልቃ ሊገባባት የማይቻል መንግስት እንዳላት መልዕክት እናቀርባለን ብለዋል።

ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር የወደብ ስምምነት መፈፀሟ የሶማሊያን መንግሥት ማስቆጣቱ ይታወሳል።

የተለያዩ ሀገራት መሪዎች አዲስ አበባ መግባት የጀመሩ ሲሆን ከእነዚህ መካከል:—
የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት
የኮትዲቫር ምክትል ፕሬዚዳንት ቲሞኮ ሚዬሊ ኮኔ ትናንት ከገቡ መሪዎች መካከል ይገኙበታል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply