የሶማሊያው ፕሬዝዳንት በኢትዮጵያ የነበራቸውን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አጠናቀው ተመለሱ

አርብ መስከረም 20 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የሶማሊያው ፕሬዝዳንት በኢትዮጵያ የነበራቸውን የኹለት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አጠናቀው ወደ አገራቸው ተመለሱ።

ፕሬዝዳንቱ በኢትዮጵያ የነበራቸውን የኹለት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የኹለቱ አገራት መሪዎች የጋራ ሥምምነቶች ይፋ አድርጓል።

ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀመድ በኢትዮጵያ የመጀመሪያቸውን ይፋዊ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን፤ ኹለቱ መሪዎች ከከፍተኛ ልዑካን ቡድኖቻቸው ጋር በቆይታቸው በቀጣናዊ እና ኹለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መምከራቸው ተገልጿል።

መሪዎቹ በትብብር ሊሰሩባቸው በሚችሉባቸው የጋራ ጉዳዮች ላይ ሥምምነት ማድረጋቸው እንዲሁም፤ የሽብርተኝነት እና የፅንፈኝነት ሥጋትን ለማጥፋት እና በኹለትዮሽ የኢኮኖሚ ትብብር ጉዳዮች ዙሪያ ተቀራርቦ ለመስራት መስማማታቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

ፕሬዝዳንቱ በኢትዮጵያ የነበራቸውን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አጠናቀው በዛሬው ዕለት ወደ አገራቸው ሲመለሱም፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ሽኝት አድርገውላቸዋል።

The post የሶማሊያው ፕሬዝዳንት በኢትዮጵያ የነበራቸውን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አጠናቀው ተመለሱ first appeared on Addis Maleda.

Source: Link to the Post

Leave a Reply