የሶማሊያ መንግስት የኢትዮጵያን አምባሳደር ከሀገር ማስወጣቱ ተሰማ

ሶማሊያ ሁለት የኢትጵያ ቆንስላ ፅህፈት ቤቶችንም ዘግታለች ተብሏል፡፡

አንደኛው ከፊል ራስ ገዝ በሆነው ፑንትላንድ እና ሌላ በተገነጠለው የሶማሌላንድ ክልል ውስጥ ይገኛል።

ይህ እርምጃ የተወሰደው ከወደብ ስምምነት ጋር በተያያዘ ውጥረቱ ተባብሶ በመገኘቱ ነው።

የኢትዮጵያ መንግሥት ትናንት የፑንትላድ ልዑካንን ተቀብሎ ማነጋገሩ በሶማሊያ ሌላ ቁጣ መፍጠሩ ነው የተሰማው።

በዚህም ዛሬ የሶማሊያ ካቢኔ ባደረገው ስብሰባ ሹመቶችን ከአፀደ በኋላ በሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር እንዲባረሩ እና ሁለት የቆንስላ ፅ/ቤቶች እንዲዘጉ ውሳኔ አሳልፏል።

በጉዳዩ ላይ የኢትዮጵያ መንግስት ያለዉ ነገር የለም፡፡

አባቱ መረቀ

መጋቢት 26 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply