የሶማሊያ እስላማዊ ታጣቂ ቡድን አልሻባብ ከዚህ በፊት ባልተለመደ ሁኔታ ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ጋር ወደ ምትዋሰንበት ግዛት ዘልቆ በመግባት ጥቃት ሰንዝሮ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሶ ነበር።…

የሶማሊያ እስላማዊ ታጣቂ ቡድን አልሻባብ ከዚህ በፊት ባልተለመደ ሁኔታ ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ጋር ወደ ምትዋሰንበት ግዛት ዘልቆ በመግባት ጥቃት ሰንዝሮ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሶ ነበር። ሰ.ሜሪካ :- ሐምሌ 15/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ እስላማዊ ቡድኑ ይህን ጥቃት ከሰነዘረ በኋላ የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ በወሰደው የመልሶ ማጥቃት እርምጃ የታጣቂ ቡድኑ አባላት ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን እና የአልሸባብ አባላት ተከበው እንደሚገኙ ምንጮች ተናግረዋል። ረቡዕ ዕለት ሐምሌ 13/2014 ዓ.ም. የአልሻባብ ታጣቂዎች ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ገብተው ጥቃት ከሰነዘሩ በኋላ ከሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል ከባድ ግጭት መካሄዱን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ገልጸዋል። እስላማዊው ቡድን አልሸባብ ከሶማሊያ ጋር ወደ ሚዋሰነው የኢትዮጵያ አፍዴር ዞን በመግባት ጥቃት ከሰነዘረ በኋላ ከባድ ጉዳት እንደደረሰበት የተነገረ ሲሆን፣ የክልሉ ልዩ ኃይል ታጣቂዎቹን በሐረገሌ ወረዳ ውስጥ በሚገኘው ሁልሁል በተባለው ስፍራ እስላማዊ ታጣቂ ቡድኑን ከበው እንደሚገኙ ምንጮች ለቢቢሲ ተናግረዋል። ለሁለት ቀናት በዚህ በአልሻባብ እና በሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል መካከል በተደረገው ግጭት አስካሁን ስለደረሰው ጉዳት የተረጋገጠ መረጃ ባይወጣም፣ ሰላማዊ ሰዎችን ጨምሮ በርካታ ተዋጊዎች መገደላቸውና ጥቂት የማይባሉ ተሽከርካሪዎች መቃጠላቸው ተገልጿል። ቢቢሲ ሶማሊኛ ያናጋራቸው አንድ የአካባቢው የፀጥታ ባለሥልጣን እንዳረጋጡት፣ የታጣቂዎቹ አባላት ሐርገሌ ወረዳ ውስጥ ሁልሁል በተባለ ስፍራ በተለይም ጎልድሂር በሚባል ቦታ ላይ ተከበዋል። ወደ ኢትዮጵያ ዘልቀው የገቡት የአልሻባብ ታጣቂዎች አላማቸው ምን እንደነበርና ወደዬት ለማምራት አስበው ጥቃት እንደከፈቱ የታወቀ ነገር የለም። ቢቢሲ ሶማሊኛ እንደዘገበው ከዚህ ጥቃት ቀደም ብሎ የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል በኤልከሬ ወረዳ ውስጥ በሚገኝ ሂሎ ማዶው በተባለ መንደር ውስጥ ባካሄደው አሰሳ በጉድጓድ ውስጥ ተቀብረው የነበሩ የተለያዩ አይነት የጦር ማሳሪያዎችን አግኝቷል። © ቢቢሲ አማርኛ ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply