የሶማሊ ክልል ከተመሰረተ ጀምሮ የነበሩ ቀበሌዎች ላይ የምርጫ ጣቢያዎች እንዲቋቋም ከተወሰነ በ6ኛዉ ሀገራዊ ምርጫ ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳለዉ ክልሉ አስታዉቋል፡፡

ሶማሊ ክልል 6ኛውን ሐገራዊ ምርጫ ላይሳተፍ እንደሚችል ከትላንትና በስቲያ በሰጠዉ መግለጫ አስታዉቋል፡፡የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአፋርና በሶማሊ ክልሎች የይገባኛል ጥያቄ በሚነሳባቸው 8 ቀበሌዎች ላይ ሊቋቋሙ የታሰቡ 30 የምርጫ ጣቢያዎችን እንዳይቋቋሙ ማድረጉን ተከትሎ ነው የሶማሊ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምርጫ የመሳተፍ ሁኔታዉን ጥያቄ ዉስጥ ያስገባዉ፡፡

የሶማሊ ክልል መንግስት ኮምኒኬሽን የሚዲያ ክትትል አስተባባሪ አቶ አብዶ ኢሌ ሀሰን ለአሀዱ ይህ ጉዳይ በድርድር ብቻ እንደሚፈታ መታወቅ ይኖርበታል ብለዋል፡፡ባለፉት 5 ምርጫዎች በሶማሊ ክልል ሥር ምርጫ የተካሄደባቸው፣ ክልሉ ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ በመስተዳድሩ ስር የነበሩት ቀበሌዎች ላይ ምርጫ ጣቢያዎች የማይቋቋሙ ከሆነ ምርጫውን ለመሳተፍ  ክልሉ እንደሚያዳግተዉ ገልጿል፡፡

የሶማሌ ክልላዊ መንግሥት የአፋር ክልል የይገባኛል ጥያቄ ባነሳባቸው 8 ቀበሌዎች ላይ የተነሳውን ቅሬታ አስመልክቶ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርዱ ደብዳቤ ቢጽፍም ቦርዱ የክልል መስተዳድሩን ሳያማክር ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ ሆኖም ከዚህ ቀደም እንደነበረዉ ቀበሌዎቹ በሶማሊ ክልል ስር ሆነዉ የምርጫ ጣቢያዉ የሚደራጅ ከሆነ ምርጫዉን ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸዉም ገልጸዋል፡፡

የተላለፈው ውሳኔም ለነባራዊ እውነታ ትኩረት የነፈገ፣ የአፋር ክልልን ያልተገባ ፍላጎት ለማስፈጸም እድል የሚሰጥ፣ የሶማሊ ክልል ሕዝቦች ላይ ቅሬታ የሚፈጥር፣ ፍትሕ ከማስፈን ይልቅ ችግሩ እንዲባባስ የሚያደርግ መሆኑ መገለጹ ይታወሳል፡፡

ቀን 18/07/2013

አሐዱ ራዲዮ 94.3

Source: Link to the Post

Leave a Reply