የሶማሌ እና የአፋር ክልሎች መወነጃጀል፡፡ (አሻራ ታህሳስ 19፣ 2013 ዓ.ም) የሶማሌ ክልል በግዛቱ በሲቲ ዞን በአፍደም ወረዳ በአፋር ታጣቂዎች በሶማሌዎች ላይ ጥቃት እንደደረሰባቸው በመግ…

የሶማሌ እና የአፋር ክልሎች መወነጃጀል፡፡ (አሻራ ታህሳስ 19፣ 2013 ዓ.ም) የሶማሌ ክልል በግዛቱ በሲቲ ዞን በአፍደም ወረዳ በአፋር ታጣቂዎች በሶማሌዎች ላይ ጥቃት እንደደረሰባቸው በመግ…

የሶማሌ እና የአፋር ክልሎች መወነጃጀል፡፡ (አሻራ ታህሳስ 19፣ 2013 ዓ.ም) የሶማሌ ክልል በግዛቱ በሲቲ ዞን በአፍደም ወረዳ በአፋር ታጣቂዎች በሶማሌዎች ላይ ጥቃት እንደደረሰባቸው በመግለጫው አሳውቋል፡፡ የአፋር ክልል ግን ጉዳዮን ሙሉ በሙሉ አስተባብሎ ጥቃት የደረሰው በአፋር ክልል በገዋኔ ወረዳ ነው፡፡ ጥቃት አድራሹም የአሸባሪ ደጋፊው እና ኮንትሮባንዲስቱ ሀይል ነው ሲል የሶማሌ ክልልን መግለጫ አጣጥሏል፡፡ የሶማሌ ክልል በመግለጫው በአፍደም ወረዳ ጥቃት አድራሾች የህወሓት ርዝራዦች ናቸው ሲል ያሳወቀ ሲሆን፣ ሁለቱም ክልሎች ባልተቋረጠ መካሰስ ላይ ናቸው፡፡ የበሰበሰው የብሄር ፌዴራሊዝም ክልሎችን እያባላ፣ የኢትዮጵያን አንድነት እያላላ ለመሄዱ አንዱ ማሳያ በሀይማኖት እና በባህል አንድ የሆኑትን የአፋር እና የሶማሌ፣ የአማራ እና የትግራይ መቃቃር ነው፡፡ በተመሳሳይ የአማራ እና የቢሻንጉል ጉምዝ ብልፅግናዎችም የተካረረ መግለጫ ሲያወጡ የሰነበቱ ሲሆን፣ በሲዳማ እና በወላይታ ተመሳሳይ መቃረን እንደነበር አይዘነጋም፡፡ በሀረር እና በኦሮሞ ክልሎች መካከልም ፣በአዲስአበባ እና በኦሮሚያ ክልል፣ በአኝዋክ እና ኑዌር መካከልም ልዮነቶች ጎልብተው እንደነበር ይታወሳል፡፡ የሶማሌ ክልል ርዕሰመስተዳድር አቶ ሙስጠፋ መሃመድ ” የብሄር ፌዴራሊዝሙ በአተገባበሩም ሆነ በሀሳቡ ካልተስተካከለ ሀገራችንን ወደ አስቸጋሪ ሁኔታ ትገባለች” ብለዋል፡፡ የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ መሪዎች ግን በብሄር ፌዴራሊዝሙ ቆርበናል እያሉ ነው፡፡ የቋንቋው ፌዴራሊዝም መቀጠል አለበት እያሉ ነው፡፡ በጠቅላላው ግን ብልፅግና አንድ ያልሆኑ ወገኖች ማህበር የመሰረቱበት ግራ ገብ ፓርቲ ነው ማለት ይቻላል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply