የሶማሌ ክልል የተፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ የአጸፋ ርምጃ እንደሚወስድ ገለጸ።

የሶማሌ ክልል የተፈጸመዉን ጥቃት ተከትሎ ማንኛዉንም አስፈላጊ እርምጃ ለመዉሰድ እንደሚገደግ ያስታወቀ ሲሆን የአፋር ክልል በበኩሉ የሶማሌ ክልል በወሰኔ ዘልቆ ያስገባውን ልዩ ሀይል በአስቸኳይ እንዲያወጣ ሲል አሳስበቧል፡፡የሶማሊ ክልል በአፍደም ወረዳ ለሄለይ ቀበሌ ንጹሀና ዜጎች ላይ የተፈጸመን ግድያ አስመልክቶ መግለጫ ማዉጣቱ ይታወቃል፡፡ክልሉ በተደጋጋሚ ሲከሰት የነበረዉን ግጭት በሰላማዊ መልኩ ለመፍታት ሰፊ ጥረት ማድረጉን ገልጾ ሆኖም አሁንም ጥቃቶች በመቀጠላቸዉ ምክንያት ክልሉ ንጹሀን የሆኑ ዜጎችን ህይወት እና ንብረት ለመታደግ ማንኛዉንም አስፈላጊ እርምጃ እንደሚወስድ አስታዉቋል፡፡

የክልሉ መንግስት ኮሚኒኬሽን ሚዲያ አስተዳደር ሀላፊ ለአሀዱ እንደተናገሩት ይህ ግጭት ከአራት ወራት በፊት መከሰቱን ጠቅሰዉ የአፋር ክልል ምንም አይነት እርምጃ ባለመዉሰዱ በድጋሚ ተፈጥሯል ብለዋል፡፡ከሰሚኑን በተከሰተው ጥቃትም ምን ያህል ሰዎች ህይወታቸዉን እንዳጡ በመጣራት ላይ መሆኑን ኃላፊው ነግረዉናል፡፡

የአፋር ክልልም የሶማሊ ክልላዊ መንግስት ያወጣዉን መግለጫ ተከትሎ ለአሀዱ በላከዉ መግለጫ  አንድ ሉአላዊ በሆነ በጋራ ሀገር ውስጥ እየኖርን ግልፅ የሆነ የጦርነት አዋጅ በይፋ ማወጁን ቀጥሏል ብሏል።

አልፎ አልፎ ይከሰቱ የነበሩ ግጭቶች ለማስቆም እና የአርብቶ አደር ማህበረሰቡን በአብሮነትና በጋራ ህይወቱን እንዲቀጥል ለማስቻል የተደረሰበትን ስምምነት ወደ ጎን በመተው ግልፅ የጦርነት አዋጅ በወንድማማች ማህበረሰብ ላይ የሶማሊ ክልል አዉጃል ሲልም በመግለጫዉ ጠቅሷል፡፡ የአፋር ክልል ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ አቶ አህመድ ከሌታ ለአሀዱ የሶማሌ ክልል ያወጣዉ መግለጫ የጦርነት አዋጅ ነዉ በማለትም ገልጸዋል፡፡

*************************************************************************************

ዘጋቢ፡ቤዛዊት ግርማ

ቀን 20/04/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply