የሶማሌ ክልል ድርቅ

ሶማሌ ክልል ውስጥ በተባባሰው ድርቅ ወደ 2.4 ሚሊዮን የሚሆን ሰው ለችግር መጋለጡ ተነግሯል።

የክልሉና ፌደራል መንግሥት፣ እንዲሁም በውጭ የሚኖሩ የክልሉ ተወላጆች ልዩ ልዩ ድጋፍ እያደረጉ ነው መሆናቸው ተገልጿል።

የድርቅ ተጎጂዎቹ ለራሳቸው እርዳታ፣ ለእንስሣቱ መኖ ፍለጋ ወደ ጂጂጋና በዙሪያዋ ወዳሉ ወረዳዎች እየገቡ መሆኑን የክልሉ መንግሥት አስታውቋል።

ተፈናቅለው ጂጂጋ ዙሪያ ፋፈን ዞን የገቡ አርብቶ አደሮች በ63 መጠለያ ጣቢያዎች እንደሚገኙም ታውቋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያገኛሉ።

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply