
የሸራተን አዲስ ኮንሰርት ተሰረዘ ድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ ለአዲስ ዓመት የምታቀርበውን የሙዚቃ ኮንሰርት የኃይማኖት አባቶችን ትዕዛዝ በማክበር ሰረዘች። እኔ ድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ ጳጉሜ 6 በሸራተን አዲስ ለአዲስ ዓመት ዋዜማ የሙዚቃ ስራዬን ለማቅረብ ተፈራርሜ የተዘጋጀሁ ቢሆንም ይህን ስራ በመሰረዜ የሚያስከፍለኝ ዋጋ ቢኖርም ከሁሉም በላይ በቃሏ የምመራላት ቤትክርስትያን ሀይማኖት አባቶቼን ትዕዛዝ በመቀበል የማቀርበውን የሙዚቃ ስራ ሰርዤአለሁ ! ለውድ አድናቂዎቼ እንዲሁም የፕሮግራሙ አዘጋጆች ይቅርታ እየጠየኩ በሌላ ዝግጅት እንደማስደስታችሁ እና እንደምንገናኝ ስገልፅላችሁ በታላቅ አክብሮት እና ምስጋና ነው!
Source: Link to the Post