የሸሹ የአማራ ሳይንት ካድሪዎች በአማራ ሳይንት ፋኖ እና በህዝቡ ይሁንታ ተመልሰው ወደ ቀደመ ስራቸው እንዲገቡ ቢደረግም የተባረረው የአገዛዙ ጦር ተመልሶ እንዲገባ ለማግባባት ብሎም ለማስፈራራት ጥረት እያደረጉ ነው ሲሉ አወገዙ። አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ሰኔ 21/2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ የሸሹ የአማራ ሳይንት ካድሪዎች በአማራ ሳይንት ፋኖ እና በህዝቡ ይሁንታ ተመልሰው ወደ ቀደመ ስራቸው እንዲገቡ ቢደረግም የተባረረው የአገዛዙ ጦር ተመልሶ እንዲገባ ለማግባባት ብሎም ለማስፈራራት የሚያደርጉትን ጥረት ያወገዙት ነዋሪዎች አሁንም በሰላም እየኖረ ያለን ህዝብ ትጥቅ እናስፈታለን በሚል የሚመጣን ኃይል አንቀበልም፤ ሞፈር ቀንበራችን እየተውን እናንተን ጭምር እንታገላችኋለን ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። አማራ ሳይንትም ሆነ መላው አማራ ማዳበሪያ እና ምርጥ ዘር ሊቀርብለት በሚገባው ሰዓት ጥይት እና ቦምብ ይዛችሁ የምትመጡ የኦህዴድ ብልጽግና ስልጣን አስጠባቂ ኦነጋዊ ኃይሎችን አንቀበላችሁም ሲሉ ነው ነዋሪዎቹ መልዕክት ያስተላለፉት። መስተዳድሩ ማዳበሪያ እየሰጣችሁ አሳምኑ የተባሉ ካድሪዎችም ከሰኔ 18/2015 ጀምሮ ሽማግሌዎችንና በየቀበሌው ህዝቡን በመሰብሰብ “እባካችሁ እኛ በአመራርነታችን ተወቅሰናል፤ እባካችሁ ገብተው ይውጡ!” በማለት ለማታለል እና ለማስፈራራት እየሞከሩ ነው ተብሏል። “እናንተ ባትፈቅዱ በኃይል ይገባል፤ ጉዳት እንዳይደርስ” እያሉ ለማስፈራራት ሲሞክሩም “በኃይል የሚመጣን አካል መቀበል የአማራ ሳይንት ታሪክ ስላልሆነ ይምጣ መልሱን ለህዝቡ እንተዋለን” የሚል ምላሽ የተሰጣቸው ስለመሆኑ ለማወቅ ተችሏል። በመጀመሪያም አዛዡ ህዝቡን ለማነጋገር ከፈለገ ከእነ አጃቢዎቹ በመምጣት መስራት ሲገባው ከ17 በላይ መኪና ሙሉ ጦር ይዞ በመምጣት አጅባር ላይ ከቤተ ክርስቲያን ጎን ምሽግ መቆፈር አይገባውም ነበር ሲሉም ነዋሪዎች ወቅሰዋል። በመሆኑም ጦሩ የሚመጣው ትጥቅ ለማስፈታት እና ለማፈን እየመጣ ስለመሆኑ በሌሎች የአማራ ጨአካባቢዎች እያደረገው ካለው የአፈና እንቅስቃሴ ለመረዳት መቻሉን ገልጸዋል። ይህን ተከትሎም በለጩማ በመግባት ሰኔ 20/2015 ከሚሊሾች ጋር የተነጋገረው እና ለአፈና ወደ አጅባር አቅንቶ በህዝቡ የተመለሰው ጦር ሁኔታውን በማዬት መመለሱ ተሰምቷል። ጥቁር ክላሽ እና የቡድን መሳሪያ የያዙ ፋኖ ልጆቻችሁን እንዲመልሱ አድርጉልን በማለት ሽማግሌዎችን እየጠየቁ ስለመሆኑም ለማወቅ ተችሏል። አመራሩ ለመግባት የሞከረውን ጦር ከአማራ ሳይንት አጅባር በመመለስ ረገድ እጃቸው ነበረበት በሚል ሚሊሾችን፣ የፖሊስ አባላትን እና ከህዝቡም ተሰሚነት ያላቸውን ሰዎች በመለዬት ጭምር መከላከያ ሲገባ በህግ እንዲጠየቁ እናደርጋለን የሚል የተሳሳተ አካሄድ ላይ ስለመሆናቸው የጠቆሙት የመረጃ ምንጮች “ዛሬም እንደ ትናንቱ አማራ ሳይንት ከህዝብ ፍቃድ እና ይሁንታ ውጭ አይደፈርም፤ መብቱን በመጠየቁም አንድ አማራን እንኳ አያስነካም፤ አሳልፎም አይሰጥም፤ አሁንም የወረዳ አመራሮች ከፈለጋችሁ ከስህተታችሁ ተምራችሁ ከጠላት ጋር ሳትወግኑ እንድትሰሩ ከህዝብ የተሰጣችሁን ተደጋጋሚ እድል ሳታባክኑ ብትጠቁበት ይሻላችኋል” ሲሉ መልዕክታችን አስተላልፈዋል።
Source: Link to the Post