የሸኔ ቡድን በምዕራብ ወለጋ በዜጎች ላይ አደጋ እያደረሰ በመሸሽ ላይ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕከት “…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/DeZOhj7bKjxqM4VlE7SG399AeTs9fPIp51YWEQQA8pjVZu0xOyfRWqwJeJL9PidTOFsQmlWjscHLYTR4_mhTthAgfJ_-2No3hVcvi7JDrE_V0ln8Zg-tuYRK0C-1tTee8MYbamBUVusQ3uaIqwXgQsgrlPkKJnrvCDVgz_8EhiA-XfvcJpcN2GLAxQ3oYm54xme6-G7f8PSEdRebf31olu5e3gvgNKCPCery9_G6lkD60JCTGAmHLnr_t7Ldk4CBDiMYHBZmKfc2CzMIXjo5qwwU6L32ZTXtRQxyJZOS9yxPk9kmsT8tuxxwSMbMivvjbO4_p-SgGKKB3zuhj6e8OA.jpg

የሸኔ ቡድን በምዕራብ ወለጋ በዜጎች ላይ አደጋ እያደረሰ በመሸሽ ላይ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕከት “የጸጥታ አካላት ከሚያደርሱበት ዱላ የፈረጠጠው የሸኔ ቡድን በምዕራብ ወለጋ በዜጎች ላይ አደጋ እያደረሰ በመሸሽ ላይ ነው” ብለዋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል፣ ቄለም ወለጋ ውስጥ የሚገኙ ዜጎች ጭፍጨፋ ተፈጽሞባቸዋልም ነው ያሉት፡፡

“በዜጎቻችን ላይ በደረሰው መከራ እያዘንን ይሄንን አሸባሪ ቡድን እስከመጨረሻው ተከታትለን ከሕዝባችን ጋር እናስወግደዋለን” ሲሉም ገልጸዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሰኔ 27 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply