You are currently viewing የሸዋሮቢት ነዋሪዎች ለወለጋ ሰማዕታት ድምፅ መሆናቸውን ተከትሎ መንግስታዊ አፈና እና እስር እየተፈጸመባቸው መሆኑ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ    ሰኔ 24 ቀን 2014 ዓ.ም…

የሸዋሮቢት ነዋሪዎች ለወለጋ ሰማዕታት ድምፅ መሆናቸውን ተከትሎ መንግስታዊ አፈና እና እስር እየተፈጸመባቸው መሆኑ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሰኔ 24 ቀን 2014 ዓ.ም…

የሸዋሮቢት ነዋሪዎች ለወለጋ ሰማዕታት ድምፅ መሆናቸውን ተከትሎ መንግስታዊ አፈና እና እስር እየተፈጸመባቸው መሆኑ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሰኔ 24 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በሸዋሮቢት የወለጋ ሰማዕታትን በማሰብ የተደረገውን የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ መንግስታዊ አፈና እና እስር መቀጠሉ ተገልጧል። እስሩም በዋናነት:_ በሸዋሮቢትና አካባቢው የሚኖረውን ማህበረሰብ የሚያነቁ፣ ከመንግስት ርዕዮተዓለም በተቃራኒው በፖለቲካው መድረክ የሚሳተፉ፣ በሲቪል ሰርቢስ ተቀጥረው በመንግስት መስሪያ ቤት ውስጥ በሙያቸው እየሰሩ በህልውና ትግሉ እየተሳተፉ ያሉትን፣ ፋኖንና ተፎካካሪ ፓርቲን በፋይናንስ የሚያግዝ ባለሀብትና ነጋዴ እና በተለያዩ የአመራር ወንበር ላይ የተቀመጡ ነገርግን የኦሮሙማ የበላይነትን ያልተቀበሉ ሰዎችን ለይተው ስም ዝርዝር በመያዝ መሆኑ ተገልጧል። በመረጃው ላይ በዋነኝነት የፋኖ አመራሮችንና አባላትን ትኩረት እንደሚሰጡ ተቀምጧል። በአቋማቸው ይፀናሉ ተብለው የተገመገሙትን ደብዛቸውን ለማጥፋት በእቅዱ ውስጥ ተይዟል። በጣም የሚያሳዝናው የአፋኙ ስርዓት አስፈፃሚ አመራሮች በግል ቁርሾ የሚፈልጓቸውን በትግሉ ውስጥ ተሳትፎ የሌላቸውን ግለሰቦች አብረው ለማጥፋት አሲረዋል ስለማሴራቸውም እየተነገረ ነው። ለወለጋ ሰማዕታት የተደረገውን የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ አስተባብራችኋል በሚል ከታሰሩት መካከል:_ 1) ወጣቱ ታጋይ እና ብዕረኛ አዶናይ አበበ እና 2) የመንግስት ሰራተኛው ያሬድ ሙሉነህ ይገኙበታል። አዶናይ አበበ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ጠንከር ያሉ መንግስትን የሚተቹ መልዕክቶችን በማስተላለፍ ይታወቃል። እንደአብነትም የወለጋ ሰማዕታትን ተከትሎ:_ “ይህ የከረፋ ስርዓት አንድ ቀንም መቆየት ሲበዛበት ነው። የህዝብ ደህንነት መጠበቅ ዝቅተኛው የመንግስት ኃላፊነት እንደሆነ ይታወቃል። በየቀኑ እየተገደልን ልንኖር አንችልም። የአንድ ቀበሌ ም/ሊቀመንበር በትርፍ ጊዜው ሊሰራ የሚችለውን ችግኝ ተከላ የመንግስት ወነኛ ስራ አድርጎ የሚቆጥር ስርዓት ለኢትዮጵያ አይመጥናትም።” በሚል Adonay Abebe በተሰኘው ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ አስፍሯል። ቀደም ሲል ደግሞ “ገዳዩና ጨፍጫፊው የአብይ አህመድ መንግስት መሆኑን ያላመነ አማራ ሲጮኽ ይኖራል እንጂ ነፃ አይወጣም።” ሲል አስፍሯል። የታሰሩት በአስቸኳይ እንዲፈቱም የሸዋሮቢት ነዋሪዎች ፖሊስ ጣቢያ ድረስ በመሄድ እየጠየቁ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply