የሸዋ ተፈናቃዬች! የወያኔ የጦር አበጋዞች መንግሥት! የትግራይ ህዝብ በስብዓዊ ጋሻነት!!! ፀ/ት ፂዮን ዘማርያም

‹‹የነገ ሞች ዛሬ አስክሬን ይሸኛል›› አቡነ ማቲያስ፣የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መሪ
ዓሳራ ግመል
አንድ የትግራይ ተወላጅ ምሁር በአንድ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር መጠረት ወያኔ ይሄን ለምን እንደማይቀበለው እንገንዘብ፤“የህወሓት/ማሌሊት መሪዎችና ካድሬዎቻቸው ሌላ አማራጭ መንገድ የማያውቁ በስታሊናዊ ጨካኝ አስተሳሰብ ተኰትኩተውና እንደ ዓሳራ ግመል ፊታቸውን ተሸብበው ያደጉ ናቸው:: መለስ ዜናዊም ብልጥ ነው:: ሆን ብሎ የህወሓት/ማሌሊት ሶፍት ዌር ፕሮግራም በጭንቅላታቸው ውስጥ የገጠመላቸው ስለሆኑ ከዚያ አጥር ወጥተው ሌላ ሰፋ ያለ ዓለምና ሳይንስ የሚያዩበት መነፅር የላቸውም:: ቢተኩሱም! ቢነግሱም! ቢማሩም ያው ናቸው ምንም አይለወጡም:: ቀደም ብሎ በአእምሮኣቸው ከተገጠመላቸው የሶፍት ዌር ፕሮግራም ውጭ ሌላ የሚያውቁትና የሚናገሩት ሰላማዊ ቋንቋ የላቸውም:: ሁሉ ጊዜ “አካኪ ዘራፍ!! በለው ደምስሰው!! – ያዘው ልቀቀው” የሚሉትን ቃላቶች ብቻ ናቸው በአእምሮኣቸው የሚታዩባቸው:: ሕግ አይገዛቸው! ባህል አይገዛቸው! ታሪክ አይገዛቸው! ሀይማኖት አይገዛቸው! ጊዜ አይለውጣቸው! ዕድሜያቸው ልክ አንድ ዓይነት መዝሙር እየዘመሩ ጭንቅላታቸውን በማሌሊታዊ ሰይጣናዊ አስተሳሰብ እንደተቆለፈ ያልፋሉ:: በመሆኑም አሁን እየታየ ያለው ትልቁ አሳሳቢ ጉዳይ የህወሓት መሪዎችና ካድሬዎቻቸው በማሌሊት ሶፍት ዌር ፕሮግራም መደንዘዛቸው ብቻ አይደለም ችግሩ:: ነገር ግን ከጫካ ይዘውት የመጡት መድሃኒት አልባ በሽታ ወደ ሌሎች ክልሎችም በፈጣን ሁኔታ እየተዛመተ መምጣቱ ነው:: ስለዚህ “ቤቱን ሳይቃጠል በቅጠል” እንደተባለው እኛም በተራችን ሳንታመም የመከላል ዘዴ መፍጠር ይኖርብናል፡፡”

የወያኔ የጦር አበጋዞች መንግስት የፖለቲካ ሥልጣናቸውን በሰላማዊ መንግድ ያሸጋግራሉ ብሎ መጠበቅ ከእባብ እንቁላል እርግብ ይፈለፈላል ብሎ እንደመጠበቅ ይቆጠራል፡፡ በዴሞክራሲ ስም አንባገነንነት፣ በነፃነት ስም ባርነት፣ በፍትህ ስም ኢፍህታዊነት፣ በብልፅግና ስም ድህነት፣ መርሃቸው ያደረጉ በዘር ፖለቲካ የተደራጁ የጦር አበጋዞች በየክልላቸው የራሳቸውን ዘውድ ጭነው በዴሞክራሲ፣ በእኩልነት፣ በፌዴራሊዝም ስም፣ በህገመንግሥት ስም አስሬ ይምላሉ ይገዘታሉ፡፡ ህወኃት በ45 ዓመታት የፈጸማቸው ወንጀሎች ተቆጥረውና ተዘርዝረው አይዘለቁም፡-
{1} በትግራይ ክልል ብዙ የትግራይ ተወላጆችን፣ የኢዲዩና የኢህአፓ/ኢህአሠ ሰራዊትን ገድለው ቆፍረው የቀበሩበት የጅምላ መቃብሮች ቦታዎች ይገኛሉ፡፡ ወያኔ የኢዲዩ አባላቶችን አስሮ ካሰቃያቸው በኃላ በነፍሰ ገዳይ ስኮዶቹ በነ ደብረጺዮንና ብስራት አማረ አማካኝነት ረሽነዋቸዋል፡፡
{2} የኢህአፓ አመራር አባሎችን እነ ፀጋዬ ገብረመድህን (ደብተራው)ና ሎሎችን ከመቀሌ እስር ቤት አስረው ካስቃቸው በኃላ ረሽነዋቸዋል፡፡ ለዚህ ግድያ ተጠያቂዎቹ የህወኃት አመራሮች ስብሃት ነጋ፣ መለስ ዜናዊ፣እስዬ አብርሃ፣ አባይ ፀኃዬ ወዘተርፈዎች በደም የተጨማለቁ ነፍሰ ገዳዬች መሆናቸውን አንርሳ፡፡
ህወኃት የጦር አበጋዞች መንግስት የፖለቲካ በትረ ሥልጣን ከያዙ በኃላ በሃገሪቱ የተለያዩ ክልሎች ውስጥ የጅምላ ግዳያዎች በመፈፀም እጃቸውን በደም የታጠቡ ብድኖች ናቸው፡-
{3} በኦሮሚያ በወለጋ፣ በበደኖ፣ በባሌ ከያዶት ወጣ ብሎ ብዙ ሰዎች ገድለው በግሬደር ቆፍረው የቀበሩበት የጅምላ መቃብሮች ቦታዎች ይገኛሉ፡፡
{4} በሱማሌ ክልል ብዙ ሰዋች በኦብነግ ሥም ገድለው በግሬደር ቆፍረው የቀበሩበት የጅምላ መቃብሮች ቦታዎች ይገኛሉ፡፡
{5} በአማራ ክልል ብዙ የወልቃት ተወላጆችን ገድለው በግሬደር ቆፍረው የቀበሩበት የጅምላ መቃብሮች ቦታዎች ይገኛሉ፡፡
{6} በጋምቤላ ክልል ብዙ የአኝዋክ ተወላጆችን እነ አባይ ፀሃዬና ዶክተር ገብርአብ በርናባስ ገድለው በግሬደር ቆፍረው የቀበሩበት የጅምላ መቃብሮች ቦታዎች ይገኛሉ፡፡
ህወሓት ለትግራዋይ የማንነት መታወቂያ የሚሠጥ የንግድ ድርጅት ነው፡፡ ወያኔ አመሰራረቱ፣ በአስር ግለሰቦች በደደቢት በርሃ በቡድን የተደራጁ ግለሰቦች የግል ፍልጎታቸውንና ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ሲሉ የቡድን የማንነት ጥያቄን በማራገብ የትግራይ ዘውጌ ብሄርተኛነትን በህዝብ ላይ በኃይል የጭኑበት ስርአት ነው፡፡ የወያኔ ጦር አበጋዞቹ ህወሓት/ኢህአዴግ አመራሮች ከሚኒሊክ ቤተ መንግሥት የሥልጣን መንበራቸውን ለ27 አመታት አስጠብቀው በመሸነፍ መቀሌ ከመሸጉ ሁለት አመታት አለፋቸው፡፡ ወያኔ በተለይ ተለዋዋጭ ሁኔታዎቹን ሁሉ በመጠቀምና ያለውን ክፍተት፣ልዩነትና ጥላቻን በማራገብና እንዲሁም አዲስ ልዩነቶችን በመፍጠር በኃይል በመጠቀም አዲስ ዘውጌ ብሄርተኛነትን ይፈበርካሉ፡፡ ከመቐሌ ማዘዣ ጣቢያቸው ሆነው ተላላኪ ዎቻቸውን በማሰማራት አዲስ በደል በአለፉት ሁለት አመታት ፈፅመዋል፡፡ አንድ ሚሊዮን የኦሮሞ ህዝብ ከሱማሌ ክልል ተፈናቅለዋል!!! የሱማሌ ህዝብ ከኦሮሞ ክልል ተፈናቅለዋል፡፡ ግማሽ ሚሊዮን የአማራ ህዝብ ከተለያዮ ክልሎች ተፈናቅለዋል!!! በደቡብ ክልል 450 ሽህ ጌዲዬ ህዝብ ተፈናቅለዋል!!! የወያኔ መንግሥት የከፋፍለህ ግዛ ዘመን አብቅቶል!!! የወያኔ ታሪክ ኤርትራን ያስገነጠለ፣ የባህር በር ሃገሪቱን ያሳጣ፣ ባድሜን አሳልፎ የሸጠ መሰሪ ድርጅት ነው፡፡ የወያኔ ለኮንትሮባንድ ንግድ ሲባል ህዝብ አፈናቅለዋል፣ ህገወጥ የመሣሪያ ዝውውርና የገንዘብ ዝውውር በማድረግ ሃገሪቱን ለማመስ ሞክሮል፡፡ ወያኔ የዘረፈውን ወርቅና ገንዘብ በመቐለ አስቀምጦል፣ በብዙ ኮንቴይነሮች የተሞሉ የመቶና ሃምሳ ብር ኖቶች በማከማቸት በሃገሪቱ የፋይናንስና ባንክ የገንዘብ ዝውውር ላይ ተፅዕኖ በመፍጠር ከፍተኛ ሴራ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ የሸዋ ተፈናቃዬች! የወያኔ የጦር አበጋዞች የትግራይ ህዝብ በስብዓዊ ጋሻነት ይዘዋል፡፡ የትግራይ ህዝብ ከኢትዮጵያ ወንድሞቹና እህቶቹ ጎን ቆሞ ወያኔን የሚፋለምበት ጊዜ አሁን ነው እንላለን፡፡ ያረጀና ያፈጀው የወያኔ ሥርዓት በትግራይ የዲጅታል ቴክኖሎጅ ዘመን ወጣቶች ትግል ይገረሰሳል!!!

ተፃፈ ግንቦት 20 ቀን 2012

Leave a Reply