የሸዋ ፋኖ ህዝባዊ ሰራዊት ባሁኑ ሰአት እንደ ማህበረሰብ ከሁሉም አቅጣጫ የተጋረጠብንን የህልውናና የመጥፋት አደጋ ለመከላከል ተመስርቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጳጉሜ 1 ቀን 20…

የሸዋ ፋኖ ህዝባዊ ሰራዊት ባሁኑ ሰአት እንደ ማህበረሰብ ከሁሉም አቅጣጫ የተጋረጠብንን የህልውናና የመጥፋት አደጋ ለመከላከል ተመስርቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጳጉሜ 1 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ወጣቶች ማህበር በሸዋ_በሸዋ የፋኖ ሕዝባዊ ኃይል ያለበትን ሁኔታ በተመለከተ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ እንደሚከተለው አጋርቷል:_ የሸዋ ፋኖ ህዝባዊ ሰራዊት ባሁኑ ሰአት እንደ ማህበረሰብ ከሁሉም አቅጣጫ የተጋረጠብንን የህልውናና የመጥፋት አደጋ ለመከላከል የተመሰረተ ህዝባዊ ሀይል ነው። ይህም ሃገርን ከመበታተን ትውልድን ከመጥፋት የሚታደግ በስነ ልቡናው የጠነከረ መካች ፋኖ ህዝባዊ ሰራዊት በሁሉም አቅጣጫ የማደራጀት ስራው እየተከናወነ ይገኛል ። አሁን ያለንበት ወቅታዊ ሁኔታ ኢትዮጵያ እንደሃገር አማራው በዘር በማንነቱ ሃገራዊ ሞራላዊ ስነ ልቡናዊ አካላዊ ጥቃት በመፈፀም ወገናችን ለዘር እንዳይተርፍ አድርገው ለማጥፋት ቆርጠው የተነሱ ጠላቶቻችን ህያው ሆኖ በሚኖረው የቀደመ በማይሰበርና በማይሸነፍ ማንነታችን ጠላቶቻችንን እስከወዲያኛው ላይመለሱ አድርገን ቀብረን እኛ መስዋት ሆነን ሃገራችንንና ወገናችንን በክብር ወደፊት እናስቀጥላለን እንጂ በፍፁም አንገቱን ደፍቶ የሚቀር ትውልድም የሚፈርስ ሃገርም አይኖረንም። ሃገራችንን የቀደመ ታሪኳን ባህሏን ሀይማኖቷን ለማበላሸት በዘመናችን የተነሳው የሀገር ውስጥ ባንዳ በተለያየ አቅጣጫ ሌሎች ኃይላትን በመጠቀም በተለይ አማራውን በመጨፍጨፍ እረፍት በመንሳት በተለያየ መንገድ ለማጥፋት የተያያዙት ቢሆንም እነዚህ ግፈኞች ግን በእኛ አስተማማኝ የእውነትና የፍትህ ክንድ ይጠፋሉ እንጂ በእነዚያ ልቡሳነ ስጋ የሃገር ውስጥ ባንዳዎች ፈፅሞ አንጠፋም። ስለሆነም መላው የአማራ ህዝብ ሴት ወንድ ወጣት አዛውንት ሳይል ለሃገር ጋሻ ለወገን ጥላ የሆነውን የፋኖ አደረጃጀት በመቀላቀል በቂ ስልጠና በመውሰድ በደምና በአጥንታችን በደማቅ ቀለም የሚፃፍ የዘመኑን ታሪካዊ አሻራ ፅፈን ማለፍ ግድ ነውና እኛም ይህንን በመረዳት የአቅማችንን ለሰልጣኞች አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ እንገኛለን ። የሸዋ ፋኖ ህዝባዊ ሰራዊት አደረጃጀት ዋነኛ ዓላማ አድርጎ የተነሳበት ምክንያት ከላይ እንደተገለጠው ሃገርን ከወራሪ ህዝብን ከጥፋት መታደግ ነው። አሁን ደግሞ ባለው ነባራዊ ሁኔታ መላው አማራ በተለያየ መልኩ ጦር ተሰብቆበታል። ይሄንን የመቀልበስ ታሪካዊ ኃላፊነት ስላለብን ለዚህ የትግል ጉዞ የምናደርገውን ጥረት በመደገፍ ተያይዘን ሃገርና ወገን ትውልድ የማዳን ዘመቻውን ፍፁም በሆነ እምነት መቀላቀል ይገባል ተቀላቅለናልም። እንደ ከብት የሚታረደው አማራ አንገቱ በግፍ የሚቀላው አማራ ማኅፀን እየተሸለቀቀ ለከፋ ሰቆቃ የተሰናዳው አማራ በእኛ መራር ትግል ነፃነቱ ሊታወጅ ይገባል። ይህንን ነብሰ በላ አውሬ ከተፈጥሮ ህግ ውጭ የሰው ደምና ስጋ ለሚመገብ ሰው መሣይ አውሬ የቅጣት ክንዳችን ሊያርፍበት ይገባል። በቃ በገዛ ሀገራችን ላይ ለቅሶ ኃዘን መከራው ስደቱ መንገላታት ንብረት መውደሙ መፈናቀሉ ርሀብ ጥሙ በቃ ልንል ይገባል። ይህንን ባንዳ ሀገር አፍራሽ የንፁሃን ደም ጠጪ አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ፈር ማስያዝ ይገባል። አማራን በማጥፋት ኢትዮጵያን ማፍረስ እቅድ አድርጎ የተነሳን ጠላት ምህረት በሌለው ክንዳችን ደቁሰን ነፃነቷ የተረጋገጠ ሰላሟ የማያጠራጥር ሃገር ለቀጣዩ ትውልድ የማስተላለፍ ታሪካዊ ኃላፊነት አለብን። እኛ ሞተን በሕይወት የምትቆይ ሃገር ልትኖረን ያስፈልጋልና ስስት የሌለበት ጊዜና ሕይወት ልንሰጥ ቆርጠን ተነስተናል ። የተከበርከው የሸዋ ህዝብ ሆይ በሸዋ ላይ እየተንቀሳቀሰ የመጣውን የሸዋ ፋኖ አደረጃጀት በመቀላቀል የድርሻህን በመወጣት ሁሉን አቀፍ ትግል ለማድረግ ራስህን አዘጋጅ። ይህ የማይሆን ከሆነ ካለፈው ይልቅ የሚመጣው የከፋ ይሆናልና ራሳችንን ከሽንፈት ብሎም ከውርደት የምንታደገው ገፊዎችን በደንብ መግፋት ስንችል መቅጣት ስንችል ብቻ ነው። ለዚህም አስተማማኝ የሆነ ብርቱ የህሊና ንቃት እና ፈርጣማ ጡንቻም ጭምር ያስፈልጋል። ይህ የሸዋ ፋኖ ህዝባዊ ሰራዊት አደረጃጀቱ በዋናነት መዋቅሩን በአጣዬ ማጀቴ በሸዋሮቢት አንፆኪያና ምንጃር የተዘረጋ ሲሆን በቀጣይ በመርሐቤቴ፣ መንዝ፣ እንሳሮ ጅሁር እና በሌሎች የሸዋ ግዛቶች አደረጃጀቱን የምንቀጥል ይሆናል። በዚህም የወጣቱ ቀና ትብብርና ወቅታዊው አስገዳጅ ሁኔታ ጠርቷቸው ለስራው ቅልጥፍና ምቹ መሆን ይጠበቅባቸዋል። መልካሙ የተጋድሎ ታሪካችን በታሪክ ሲዘከር የሚኖረው ዛሬ በምናደርገው የወራራ ትግል ነውና ሞትም ጀግንነትም ሜዳው ሲሆን ያምራልና ለዚህ ወሳኝ ጊዜ የማይሰጥ ምዕራፍ የተሰናዳን እንድንሆን ስንል በሸዋ ፋኖ ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply