You are currently viewing የሻምበል መማር ጌትነት ስርዓተ ቀብር በትውልድ አካባቢው በመርዓዊ ከተማ ተፈጽሟል።  አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   ጥቅምት 27 ቀን 2015 ዓ.ም        አዲስ አበባ ሸዋ  ሻምበል መማር…

የሻምበል መማር ጌትነት ስርዓተ ቀብር በትውልድ አካባቢው በመርዓዊ ከተማ ተፈጽሟል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 27 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ሻምበል መማር…

የሻምበል መማር ጌትነት ስርዓተ ቀብር በትውልድ አካባቢው በመርዓዊ ከተማ ተፈጽሟል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 27 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ሻምበል መማር ጌትነት በቅጽል ስሙ ቫንዳም ጥቅምት 18/2015 ከረፋዱ 4 ሰዓት ላይ በአሰቃቂ መልኩ በጥይት እና በስለት ጭምር ተገድሎ ተጥሎ ከተገኘበት ከወሎ መቄት ወረዳ አስከሬኑ ወደ ባህር ዳር ከዛም ወደ ትውልድ አካባቢው መርዓዊ ጥቅምት 26/2015 ሽኝት የተደረገለት መሆኑ ይታወቃል። የሻምበል መማር ጌትነት አስከሬን በትውልድ ቀዬው መርዓዊ ከተማ ከተወሰደ በኋላ ወዳጅ፣ዘመዶቹ እና የትግል አጋሮቹ በተገኙበት በሀዘን እንጉርጉሮ፣ በፉከራ፣ በሽለላ እና ደማቅ ወታደራዊ ስነ ስርዓት ታጅቦ ስርዓተ ቀብሩ ጥቅምት 27/2015 ዓ/ም በቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ተፈጽሟል። በስርዓተ ቀብሩም የሻምበል መማር ጌትነት የህይወት ታሪክ ቀርቧል፤ በ44 ዓመቱ በግፍ የተገደለው ሻምበል መማር ባለትዳር፣ የአንድ ወንድ እና የአንድ ሴት በድምሩ የሁለት ልጆች አባት እንደነበር ተገልጧል። “ሻምበል መማር ጌትነት እንኮራብሃለን፤ አልቅሰን ሳይሆን ፎክረን እንሸኝሃለን!” በሚል ከተነበበው አሻራ ሚዲያ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ ካጋራው የስርዓተ ቀብሩን ሁኔታ ከሚያሳዬው ቪዲዮ የህይወት ታሪኩ አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) እንደተረዳው ከሻምበልነት ወደ ሻለቃነት መዓረግ ለመሸጋገር ሁለት ሳምንት ብቻ ሲቀረው የወያኔ የግፍ አገዛዝ እና አድሎአዊ አሰራርን በመቃወም በራሱ ፍቃድ በ2009 ዓ/ም ከመከላከያ ሰራዊት የለቀቀ መሆኑን ነው። ሻምበል መማር ጌትነት በወቅቱ ከሰራዊቱ ሲለቅም በሰራዊቱ ውስጥ የአማራ ተወላጆች ቁጥር እንዲቀንስ አልመው ሲሰሩ የነበሩ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች እጅግ ደስተኛ ነበሩ ተብሏል። ወቅቱ የአማራ ብሄርተኝነት እያቆጠቆጠ የመጣበት ጊዜ ስለነበር ከቦታ ቦታ እየተዘዋወረ የአማራ ወጣቶችን በማንቃት እና በማደራጀት ላይ ሳለ የአማራ ክልል የልዩ ኃይል ፖሊስ ሲጠናከር ለልዩ ኃይሉ ኮሚሽነር ወታደራዊ አማካሪ በመሆን ተመድቦም ሲያገለግል ነበር። የአማራ ልዩ ኃይል በስፋት እንዲመለመል፣ እንዲደራጅ፣ እንዲሰለጥንና ክልሉን እንዲታደግ የራሱን አሻራም አበርክቷል። ሻምበል መማር በተለያዩ ጊዜያት ከተለያዩ ከፍተኛ የጦር አመራሮች ሽልማት የተበረከተለት ሲሆን የወጣትነት እድሜውን፣ ላቡንና ደሙን ለአማራ ብሎም ለኢትዮጵያ ህዝብ ሲል ሳይሰስት የሰጠ ጀግና የጦር መኮንኖች ተምሳሌት እንደነበር ተገልጧል። በተለይም ከሌሎች ተቆርቋሪ ወገኖችና ቤተሰቦች ጋር በመናበብ የሻምበል መማር ጌትነትን አስከሬን ከወሎ መቄት ለማምጣት ከፍተኛ ትግል በማድረግ ወደ ትውልድ አካባቢው መርዓዊ ያመጡ የከተማዋ ወጣቶች ከፍተኛ ምስጋና ተችሯቸዋል። የሻምበል መማር ጌትነት አስከሬን በሰሜን ወሎ ዞን መቄት ወረዳ ወርቅ ዋሻ በተባለ አካባቢ አስፓልት ላይ ተጥሎ መገኘቱን በመግለጽ ቤተሰቡ ነኝ የሚል አካል መጥቶ አስከሬኑን እንዲረከብ የወረዳው ፖሊስ ማስታወቁ ይታወሳል። የመቄት ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን ጽ/ቤትም በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ አጋርቶት የነበረውን የወረዳውን ፖሊስ መልዕክት ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ማጥፋቱ ሌላ አነጋጋሪ ጉዳይ እንደነበረ አይዘነጋም። በሰኔ 15/2011ዱ የባለስልጣናት ግድያ ከተከሰሱት እና “በሌሉበት” በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት እድሜ ልክ ተፈርዶባቸዋል ከተባሉት መካከል አንዱ የሆነው ሻምበል መማር ጌትነት በግፍ ተገድሎ አስከሬኑ ወድቆ የተገኘው በሰሜን ወሎ ዞን መቄት ወረዳ ወርቅ ዋሻ፣ ከደቡብ ጎንደር ዞን ጨጨሆ መድሃኒያለም አዋሳኝ አካባቢ መሆኑ በፖሊስ መመላከቱ ይታወሳል። በሻምበል መማር ጌትነት ግድያ ዙሪያ ብዙ አነጋጋሪ እና መጥራት የሚገባቸው አስተያየቶች ከተለያዩ አቅጣጫዎች እየተሰነዘሩ መሆኑ ቢታወቅም በመንግስት በኩል ግን እስካሁን አንድም የተሰጠ ምላሽ የለም።

Source: Link to the Post

Leave a Reply