የሻምቡ ከተማና የሆሮ ወረዳ ነዋሪዎች ኦነግ ሸኔን አወገዙ

የሻምቡ ከተማና የሆሮ ወረዳ ነዋሪዎች ኦነግ ሸኔን አወገዙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የሻምቡ ከተማና ሆሮ ወረዳ ነዋሪዎች ኦነግ ሸኔን በሰላማዊ ሰልፍ አውግዘዋል፡፡
ሰልፈኞቹ የሰላምና የልማት እንቅፋት የሆነው ኦነግ ሸኔን በማጋለጥ ሰላማችንን እናረጋግጣለን ብለዋል፡፡
አነግ ሸኔ በዞኑ በተለያዩ ቦታዎች በተደጋጋሚ በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ እያደረሰ ያለው ጥቃት ከኦሮሞ ሕዝብ ባሕል እና ወግ ጋር የሚጋጭ በመሆኑ ቡድኑን እናወግዛለን ብለዋል ሰልፈኞቹ፡፡
የሻምቡ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ ጥሩወርቅ በቀለ ኅብረተሰቡ ኦነግ ሸኔ እያደረገ ያለው ዘግናኝ ድርጊትን በመረዳት ለሰላሙ እና ለልማቱ ዘብ እንዲቆም ጠይቀዋል፡፡
ኦቢኤን እንደዘገበው የሆሩ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሓላፊ አቶ በቀለ ደቻሳ በበኩላቸው አነግ ሸኔ እና ደጋፊዎቹ በአገሪቱ የመጣውን ለውጥ ለማደናቀፍ የሚያደርጉትን ድርጊት ተረድተን በጋራ ሰላማችንን መጠበቅ አለብን ብለዋል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳ
የፋና ድረ ቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post የሻምቡ ከተማና የሆሮ ወረዳ ነዋሪዎች ኦነግ ሸኔን አወገዙ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply