የሽንት ቀለማችን ስለ ጤንነታችን ሁኔታ ጠቋሚ እንደሆነ ምን ያህል ያዉቃሉ?

ይህን ያሉን በቅዱስ ጳዉሎስ ሆሲፒታል የኩላሊቲ፤የፕሮስቴት እና የወንድ መረቢያ ክፍል ሃኪሚ እና በረዳት ፕሮፌሰር ማእረግ የትምህርት ክፍሉ መምህር የሆኑት ዶክተር ማስረሻ ሰለሞን ናቸዉ፡፡

ባለሙያዉ እንደሚሉት ታዲያ የሺንት ቀለም መቀየር ወይንም የሽንት ሽታ መኖር በሰዉነታችን ዉስጥ አንዳች የጤና እክል ስለመኖሩ ጠቋሚ ነዉ ብለዉናል፡፡

ሽንት ማለት ኩላሊት ደምን አጣርቶ የሚያስወጣው ክፍል ሲሆን፤ 95 በመቶ ውሀ ሲሆን ፤ 5 በመቶ የሚሆነዉ ደግሞ ኤሌክትሮላይቶችና ቆሻሻዎች ናቸዉም ብለዉናል ።

የሽንት ቀለምና መጠን፤ እየዎሰዱ ያሉትን የውሀ መጠን ፣ ምግብና ቫይታሚን ጠቋሚ ነውም ይላሉ ዶከተር ማስረሻ ።

የሽንት ቀለም ስለ ሰዎች ጤና ምን ይላል

1.ነጣ ያለ ከሆነ የሽንታችን ቀልም፤ኩላሊታችን በትክክል እየሰራና በቂ ዉሃ መኖሩን ያሳያል ብለዉናል ፡፡

2፣ የሽንታችን ቀለም በጣም ወደ ቢጫ ሲለወጥ ደግሞ ፤ የወሰድነዉ የዉሃ መጠን በቂ ያለመሆኑን ነገር ግን ኩላሊታችን ጤናማ መሆኑን ይገልፃል ፡፡

  1. የሽንታችን ቀለም ሲቀላ ወይንም የሻይ/የኮካ ኮላ መልክ ሲሆን ደግሞ ሁለት አይነት ምክኒያቶች አሉ ፡-

አንደኛዉ የተወሰኑ ምግቦች ፣ አንቲባዮቲኮች ፣ የህክምና ሁኔታዎች ለጊዜው የሽንት ቀለም ይቀይራሉ ብለዉናል፡፡

ሁለተኛዉ ሺንታችን የሚቀላበት ምክኒያት ደግሞ በህምም በተፈጥሮ የሚመጣ ነዉ ለአብነትም ፤- የሽንት ፊኛ ኢንፌክሺን፤ የፕሮስቴት በሽታ ወይንም ካንሰር ፤የሽንት ቧንቧ ጥበት፤የሽንት ፊኛ እጢ፤የኩላሊት እጢ፤የተለያዩ መዳኒቶች ለምሳሌ ከቲቢ ጋር ተያይዞ የአንታይ ታይበር ክሎሲስ መዳኒት የሚወስዱ ሰዎች እና በሰዉነታችን ዉስጥ ከደም ጋር ተያይዞ ከሚመጡ የተለያ ህመም ምክኒያት ሊቀላ ይችላል ብለዉናል ዶክተር ማስረሻ ሰለሞን ፡፡

  1. የሽንት ወደ ደመናማ ቀለም መቀየር ይሄም በሁለት መንገድ ሊመጣ ይችላል እሱም ፡-
    አንደኛዉ እና ዋነኛዉ በኢንፌክሺኖች ሲሆን ሁለተኛዉ ደግሞ በሽንታችን ላይ ያለዉ የፎስፈረስ መጠን ሲጨምር እና የኩላሊት ጠጠር ሲሰራ ነዉ፡፡

5.መግል የሚመስል ቢጫና ነጭ የተቀላቀለ ሲሆን ደግሞ የሽንት ቱቦ ኢንፌክሺን መኖሩን አመላካች ነዉ ተብሏል፡፡

ለመሆኑ ሰዎች በቀን ዉስጥ ምንያክል ዉሃ መጠጣት አለባቸዉ

ዶክተር ማስረሻ ወደ ኩላሊቶቻችን የሚደርሱ ፈሳሾች መመጠን አለባቸዉ ብለዋል፡፡

መመጠን ማይቻል ከሆነ ኩላሊታችን ማጣራት ከሚችለዉ በላይ እዲያጣራ ስለሚያደርገዉ ዲያቤቲክ ኢን ሲፒደስ ለሚባል በሽታ ተጋላጭ ያደርጋል ፡፡

ይህም ለሰዉነታችን ጠቃሚ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን እዲወገዱ በማድረግ የካሊሲዬም፤ሶዲዬምና ፖታሲየም እጥረት እዲከሰትና የንጥረ ነገር በዛባት እንዲከሰት ያደርጋል ብለዉናል፡፡

አንድ ሰዉ ኩላሊቶቹ በትክክል እስከሰሩ ድረስ በቀን ዉስጥ 2.5 ሊትር ሽንት ማምረት አለበት ይላሉ ዶክተር ማስረሻ፡፡

በመሆኑ ይህን ያክል ሽንት ለማስወጣት እንደየ አከባቢዉ ከዚህ በላይ ዉሃ መዉሰድ ተገቢ ነዉ ብለዉናል፡፡

ሆኖም አንድ ሰዉ በቀን ዉስጥ ከ 4 ሊትር በላይ ሽንት ካስወገደ ፖሊ ዩሪያ ይባላል ብለዉናል ይህም ወይ የበዛ ዉሃ ወስዷል ወይንም ደግሞ በዲያቤቲክ ኢን ሲፒደስ በሚባለዉ በሽታዎች ተጠቅቷል ማለት ነዉ ብለዉናል ፡፡

ጤነኛዉ የሚባለዉ የሽንታችን ቀለም ምንም ምርመራ ቢያስፈልገዉም ጎላ ቀለም በሌልዉና ነጣ ያለዉ ነዉ ብለዉናል ሃኪሙ፡፡

በመጨረሻም ዉሃን በአንድ ጊዜ አንድ ወይንም ሁለት ሊትር ዉሃ መጠጣታቸዉ ለሰዉነታቸዉም ሆነ ለጤናቸዉ ጥቅም የለዉም ተብሏል፡፡

ይልቁንም ሰዎች ሲጠማቸዉ ብቻና በየሁለት ሰዓቱ አለፍ አለፍ እያረጉ አንድም ይሁን ሁለት ብርጭቆ ዉሃን ቢጠጡ ለኩላሊታቸዉም ለሰዉነታቸዉም ገንቢ ነዉ ብለዉናል፡፡

በልዑል ወልዴ

ሰኔ 21 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply