የሽግግር ፍትህን ለማረጋገጥ የመደበኛ ፍረድ ቤቶች አቅም እና ገለልተኝነት አሳሳቢ ነው ተባለ፡፡የሽግግር ፍትህ ሂደት ውስብስብና ረዥም ግዜ የሚወስድ ስለሆነ ገለልተኛ በሆነ የፍትህ ተቋም እን…

የሽግግር ፍትህን ለማረጋገጥ የመደበኛ ፍረድ ቤቶች አቅም እና ገለልተኝነት አሳሳቢ ነው ተባለ፡፡

የሽግግር ፍትህ ሂደት ውስብስብና ረዥም ግዜ የሚወስድ ስለሆነ ገለልተኛ በሆነ የፍትህ ተቋም እንዲሁም የምርመራ ተቋም ነው መመራት ያለበት መባሉን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡

ይሁን እንጂ አሁን መንግስት ያወጣው ፖሊሲን በመደበኛ ፍርድ ቤት ልዩ ችሎት ተመድቦለት እንደሚሰራ መገለፁ ተገቢ አይደለም ተብሏል፡፡

ከጣብያችን ጋር ቆይታ የነበራቸው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ያሬድ ሃይለማርያም አሁን ባለው የፍትህ ተቋማት የሽግግር ፍትህን ማስኬድ ይከብዳል ብለዋል፡፡

በተለይም ተቋማቱ ላይ ከሚነሳባቸው የገለልተኝነት እና የአቅም ጥያቄዎች አንፃር ጥያቄ የሚያስነሳ ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡

በአፈፃፀም ደረጃ መንግስት ከሚነሳበት ጥያቄዎች አንፃር ሀሳቡን የሚቀይር ካልሆነ ከሽግግር ፍትህ ፖሊሲዎች አንዱ ክፍተት ሆኖ የሚነሳ ነው ሲሉ ለጣብያችን ተናግረዋል፡፡

በቅርቡ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበለትን ረቅቅ ፖሊሲ ከመረመረ በኃላ መፅደቁ የሚታወስ ሲሆን ልዩ ፍርድ ቤት የሚለውን የረቂቁን ሀሳብ በመሻር በመደበኛ ፍርድ ቤት በልዩ ችሎት እዲታይ ሲል መወሰኑ ይታወሳል፡፡

በዚህ አካሄድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የፈጸሙ የኤርትራ ወታደሮች እንዴት ለፍርድ ይቀርባሉ ተብሎ ለሚነሳው ጥያቄ ወንጀሉ በኢትዮጵያ እስከተፈጸመ ድረስ የየትኛውም አገር ዜጋ ቢፈጽመው በሌሉበትም ቢሆን ችሎቱ እንዲካሄድ የፍርድ ሒደቱን ያከናውናል መባሉም ተሰምቷል፡፡

በአቤል ደጀኔ

03 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply