የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ከፍትህ ይልቅ ለፖለቲካ ጠቀሜታ እንዳይውል ስጋት እንዳላቸው የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች አስታወቁ፡፡የሽግግር ፍትህ ረቂቅ ፖሊሲ በትላትናው ዕለት በሚኒሰትሮች ምር ቤት…

የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ከፍትህ ይልቅ ለፖለቲካ ጠቀሜታ እንዳይውል ስጋት እንዳላቸው የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች አስታወቁ፡፡

የሽግግር ፍትህ ረቂቅ ፖሊሲ በትላትናው ዕለት በሚኒሰትሮች ምር ቤት ቀርቦ መፅደቁ ይታወሳል፡፡
ይህ ረቂቅ ፖሊሲ ህገ-መንግስቱ ከፀደቀበት ከ1987 ጀምሮ ያሉ ጉዳዮች ጀምሮ ይመለከታል ተብሎ የታሰበበት መሆኑ ከዚህ ቀደም ሲነገር ቆይቷል፡፡

ከጣብያችን ኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር ቆይታ የነበራቸው የሴታዊት የፃታ ፍትህ ማህበር መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ስሂን ተፈራ በዚህ ደረጃ የሰፋ ከሆነ ከፍትህ ይልቅ ለፖለቲካ ያደላ እንዳይሆን ስጋት አለኝ ብለዋል፡፡

በቅርብ ግዜ በነበሩ ጦርነቶች እንዲሁም በተለያዩ ግዜያት በነበሩ የመንግስት አስተዳደሮች የተበደሉ ዜጎች በተለይም ፃታዊ ጥቃቶች በርካታ ናቸው የሚሉት ዶ/ር ስሂን፤
“ዛሬ ላይ ጥቃት የደረሰባትም የዛሬ 29 ዓመት የተጠቃች ሴትም ፍትህ ይፈልጋሉ፣ ይሁን እንጂ በዚህ ደረጃ ወደ ኃላ መሄዱ ከፍትህ ይልቅ ፖለቲካዊ አንድምታ እንዳይኖረው ስጋት አለኝ” ብለዋል፡፡

ዶ/ር ስሂን የሽግግር ፍትህ በዋነኝነት ፃታዊ ጥቃቶችን በተመለከተ በሰነዱ ላይ የተቀመጠ ቢሆንም ስለተግባራዊነቱ ግን ጥያቄ አለን ይላሉ፡፡
በተለይም ማንኛውም ፃታዊ ጥቃቶች በወንጀል ብቻ ሊታዩ የሚገባቸው መሆናቸው ሊሰመርባቸው የሚገባ ነው ሲሉም አመላክተዋል፡፡

እንደ ዶ/ር ስሂን ሀሳብ ሀገር አሁን ጦርነት ባለበት ሁኔታ እዚህም እዚያም ግጭቶች መፈናቀሎች ባሉበት ሁኔታ የሽግግር ፍትሁ የቸኮለ ነውም ባይ ናቸው፡፡

የሽግግር ፍትህ በአንድ ሀገር በሃምሳ እና መቶ አመት አንድ ግዜ የሚደረግ በመሆኑ ከሽግግር ፍትህ ፖሊሲው ቀድሞ ሰላም እና ፖለቲካዊ ንግግሮች ቀዳሚው መሆን አለባቸው ብለዋል፡፡

በትላትናው ዕለት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ አካሂዶ በሁለት ጉዳዮች ውሳኔ ያሳለፈ ሲሆን ውሳኔ ከተላለፈበት አንዱ ጉዳይ የሽግግር ፍትሕ ረቂቅ ፖሊሲ ነው።

ምክር ቤቱም በረቂቅ ፖሊሲው ላይ ከተወያያ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

በአቤል ደጀኔ

ሚያዝያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply