የሽግግር ፍትሕ የፖሊሲ ሠነድ ያዘጋጀው የባለሙያዎች ቡድን ሥራውን አጠናቀቀ

የሽግግር ፍትሕ የፖሊሲ ሠነድ ሲያዘጋጅ የቆየው 13 አባላት ያሉት የባለሙያዎች ቡድን ሥራውን አጠናቆ መበተኑ ተገለፀ።

ሥራውን ሕዳር 2015 ዓ.ም የጀመረው የባለሙያዎች ቡድን የፖሊሲ ረቂቅ ሰነዱን የመጨረሻ ውጤት ታኅሣሥ 19 ቀን 2016 ዓ.ም ይፋ አድርጎ ነበር።

የባለሙያዎች ቡድን ተጠያቂነት ፣ እውነት ማፈላለግ፣ ምህረት ፣ ማካካሻ እና ካሳ በሚባሉት አምስት የሽግግር ፍትሕ ዐምዶች ላይ ለስምንት ወራት ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በሀገሪቱ ውይይት ማድረጉን አስታውቋል።

የባለሙያዎች ቡድን ይህ ረቂቅ ፖሊሲ ከሚኒስትሮች ምክር ቤት ይልቅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውይይት ተደርጎበት ቢፀድቅ የሚል ምክረ ሀሳብንም ለመንግሥት አቅርቧል።

ከሽግግር ፍትሕ ረቂቅ ፖሊሲ ሠነድ አዘጋጅ 13 ባለሙያዎች መካከል አንዱ የሆኑት ዶክተር ማርሸት ታደሠ የባለሙያዎች ቡድን የተሠጠውን ተግባር አጠናቆ ባለፈው ሳምንት ማስረከቡን ተናግረዋ፡፡

የካቲት 04 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply