“የቀድሞው ኢህአዴግ የአሁኑ ብልጽግና ከኖረበት ጎታች ግብሩ መፋታት ተስኖታል” ሲሉ ት/ቤታችን የፖለቲካ ማዕከል ሆኗል ያሉ የአብርሃ ጅራ ሁለተኛ ደረጃ ት/ ቤት መምህራንና ተማሪዎች ገለፁ።…

“የቀድሞው ኢህአዴግ የአሁኑ ብልጽግና ከኖረበት ጎታች ግብሩ መፋታት ተስኖታል” ሲሉ ት/ቤታችን የፖለቲካ ማዕከል ሆኗል ያሉ የአብርሃ ጅራ ሁለተኛ ደረጃ ት/ ቤት መምህራንና ተማሪዎች ገለፁ።…

“የቀድሞው ኢህአዴግ የአሁኑ ብልጽግና ከኖረበት ጎታች ግብሩ መፋታት ተስኖታል” ሲሉ ት/ቤታችን የፖለቲካ ማዕከል ሆኗል ያሉ የአብርሃ ጅራ ሁለተኛ ደረጃ ት/ ቤት መምህራንና ተማሪዎች ገለፁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 29 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ “የቀድሞው ኢህአዴግ የአሁኑ ብልጽግና ከነበረበት ጎታች ግብሩ መፋታት ተስኖታል” ያሉት በምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ የአብርሃ ጅራ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት መምህራን እና ተማሪዎች ናቸው። ት/ ቤታችንን የፖለቲካ ማዕከል እና የብልጽግና ትሸርት ማደያና መሰብሰቢያ አድርገውታል የሚሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ ዛሬ መጋቢት 29 ቀን 2013 በተደረገው ሰልፍ ምክንያት መደበኛ ትምህርት ተቋርጦ መዋሉን ተናግረዋል። ጠዋትና ከሰዓት ፎርም ለመሙላት ካቀናነው ውስን ተማሪዎች በስተቀር ሌሎች ተማሪዎች ሲጉላሉ መዋሉን ጠቅሰው ለድርጅት ቅስቀሳ በሚል እንደ ህዝባዊ በዓል ትምህርት ቤቶች ተዘግተው መዋላቸው አሳዛኝ አዙሪት ነው ብለውታል። ት/ቤቱም ፈቅዶም ይሁን ተገዶ በማያዛልቀው አጉል የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ጨዋታ ውስጥ ገብቷል ብለዋል ትምህርት ከፖለቲካ ተፅዕኖ ነጻ መውጣት አለበት የሚሉ የአብርሃጅራ መምህራንና የተማሪዎች ቅሬታም መቀጠሉን ገልፀዋል። ብልጽግና ትምህርት ቤት አዘግቶ ከየ ት/ቤቱ ያሉ ተማሪዎችንና የከተማ ነዋሪዎችን በማካተት ከሰልፍ በኋላ በአብርሃ ጅራ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት አዳራሽ ተሰብስቦ መዋሉን ነው አካሄዱ ልክ አይደለም ያሉ መምህራንና ተማሪዎች የተናገሩት። መምህራን እና ተማሪዎች ት/ቤት መዘጋት የለበትም ሲሉ ትናንት ላነሱት ቅሬታ የአብርሃ ጅራ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ሙሳ እና ምክትል ርዕሰ መምህር አቶ ሻምበል ምላሽ መስጠታቸው ይታወሳል። በምላሻቸውም ከላይ የመጣ አቅጣጫ መሆኑን ነገር ግን ት/ቤት እንደማይዘጋ አስተባብለው ነበር፤ ይሁን እንጅ በተቃራኒው ዛሬ ት/ቤት ተዘግቶ የግቢው አዳራሽም የብልጽግና ሰልፈኞች በሙዚቃ ባንድ ታጅበው ተሰብስበውበት መዋላቸውን ለመረዳት ተችሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply