You are currently viewing የቀድሞው የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ሳዲቅ አል-ማህዲ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የቀድሞው የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ሳዲቅ አል-ማህዲ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ ፣ህዳር 17 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቀድሞው የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ሳዲቅ አል-ማህዲ በኮሮና ቫይረስ ለህልፈት መዳረጋቸው ተሰምቷል።
ሳዲቅ አል-ማህዲ በተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ሆስፒታል ከገቡ ከሶስት ሳምንት በኋላ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ማለፉን ቤተሰቦቻቸው እና ብሄራዊው ኡማ ፓርቲ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል ፡፡
በህዳር ወር መጀመሪያ ላይ 21 የሚሆኑ የአል-ማህዲ ቤተሰቦች በቫይረሱ ከተያዙ በኋላ ሆስፒታል መግባታቸው ተገልጿል፡፡
የ84 ዓመቱ አል-ማህዲ በቀድሞው ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር በተመራ መፈንቅለ መንግስት ከስልጣን እስከተወገዱበት በፈረንጆቹ 1989 ድረስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ማገልገላቸው የሚታወስ ነው፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

The post የቀድሞው የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ሳዲቅ አል-ማህዲ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply