የቀድሞው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀኔራል ክንፈ ዳኘው ዛሬ ከቀትር በኋላ ከእስር ተፈተዋል።ሜጀር ጀኔራል ክንፈ ከአምስት ዓመታት የእስር ቤት ቆ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/Ffd464zGnhABlfpuqqV0wZE1-4-40Uv-b5Cmx28_xUBppxwlNkoAew4vIIwR9zvAJQmRTGsYeIpokkgHGlorHfUhDwpnME3liSt-Mn__bqPpk5Xts7TALSERPip63IkdiaeJHOVlLtYF_nEylK8M7yyYX4yXu-a0ZHyd9UWys3m7tu9JqWWig8fzYD_5Y_nj9l7xWqCxA7Go-vxgyoBXtQLFk3s7vIBqEokerqZU1O4BLDq68l5VT_XZ5fZyLcqRWkEINTGr-9PzGlhnLzDR9No-Cd03XrXDFC4CbsUrpwZgVm22T5MjibXj3rKRswrbdUxGccaabO-6U4QsP4qPWA.jpg

የቀድሞው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀኔራል ክንፈ ዳኘው ዛሬ ከቀትር በኋላ ከእስር ተፈተዋል።

ሜጀር ጀኔራል ክንፈ ከአምስት ዓመታት የእስር ቤት ቆይታ በኋላ የተፈቱት፣ ፍትህ ሚንስቴር ሜጀር ጀኔራል ክንፈ ሜቴክን በሚመሩበት ወቅት ተፈጽመዋል ያላቸውን ተደራራቢ የሙስና ክሶች ትናንት “ለሕዝብ ጥቅም” ሲባል ማቋረጡን መግለጡን ተከትሎ ነው።

ክንፈ ከሜቴክ የራዳር መሳሪያ ግዢ ጋር በተያያዘ ካሆን ቀደም የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሦስት ዓመታት እስር የፈረደባቸው ሲሆን፣ በተያዘው ሳምንት ደሞ ሜቴክ ከገዛቸው ሁለት ሆቴሎች ጋር በተያያዘ ፍርድ ቤቱ የጥፋተኝነት ውሳኔ ወስኖባቸው የቅጣት ብይን ለመስማት ቀጥሮ ተሰጥቷቸው ነበር።

መጋቢት 06 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook  https://www.facebook.com/onelovebroadcas

Source: Link to the Post

Leave a Reply