የቀድሞው የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንትን ጨምሮ ሌሎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ዋነኛ የጁንታው አመራሮች አዲስ አበባ ገቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 3 ቀን 2013 ዓ.ም አዲ…

የቀድሞው የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንትን ጨምሮ ሌሎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ዋነኛ የጁንታው አመራሮች አዲስ አበባ ገቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 3 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የቀድሞውን የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት አባይ ወልዱና ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩትን ዶክተር አብርሃም ተከስተን ጨምሮ አገር ለመበታተን ሲሰሩ ቁጥጥር ስር የዋሉ የህወሓት ጁንታ አመራሮች አዲስ አበባ ገብተዋል።  የአገር መከላከያ ሠራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስና የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ጥምር ሃይል በአገር መከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት በማድረስ አገር ለመበታተን ሲሰሩ የነበሩ የአሸባሪው ህወሓት ቡድን አባላትን ለሕግ የማቅረብ ተልዕኮ እንደቀጠለ ነው። በትናንትናው ዕለትም የቀድሞውን የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት አባይ ወልዱና የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩት ዶክተር አብርሃም ተከስተን ጨምሮ ዘጠኝ የጁንታው አመራሮች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን አሁን አዲስ አበባ ገብተዋል ሲል ኢቢሲ ነው የዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply