የቀድሞው የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮምሽነር አበረ አዳሙ አረፉ።  አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   ሚያዝያ 26 ቀን 2013 ዓ.ም         አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ሚዲያ ማዕከል ከባህር…

የቀድሞው የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮምሽነር አበረ አዳሙ አረፉ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሚያዝያ 26 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ሚዲያ ማዕከል ከባህር…

የቀድሞው የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮምሽነር አበረ አዳሙ አረፉ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሚያዝያ 26 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ሚዲያ ማዕከል ከባህር ዳር ምንጮች ጋር በነበረው ቆይታ የቀድሞው የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮምሽነር አበረ አዳሙ ማረፋቸውን ለማወቅ ችሏል። ዛሬ ሚያዝያ 26 ቀን 2013 አመመኝ ብለው ለህክምና እርዳታ በባህር ዳር ጥበበ ግዮን ሆስፒታል እንደገቡ ማረፋቸው ተገልጧል። አሚማ ለእሳቸው ቅርብ ከሆነ አመራር ደውሎም ምክንያቱም በትክክል ባያውቁትም በጥበበ ግዮን ሆስፒታል ለህክምና በሄዱበት ማረፋቸውን ገልፀዋል። የሞቱበትን ተጨባጭ ምክንያት ለማጣራት አሚማ ያደረገው ጥረት ለጊዜው አልተሳካለትም። ታምሜያለሁ ባሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ ማረፋቸው እያነጋገረ መሆኑን የገለፁት ምንጮች እስካሁን መንግስት በአሟሟታቸው ጉዳይ የሰጠው መግለጫ የለም ብለዋል። ይህ በመሆኑም ከተለያዩ አቅጣጫዎች የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡ ይገኛሉ ብለዋል። አስከሬናቸው ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ድረስ ከሆስፒታሉ አለመውጣቱ ተገልጧል። የኮምሽነሩን ማረፍ ኢትዮ 251ን ጨምሮ የተለያዩ የሚዲያ ተቋማት ዘግበውታል፤ እየዘገቡትም ይገኛሉ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply