የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ናይጄሪያ ትዊተርን በማገዷ መደሰታቸውን ገለፁ፡፡

ፕሬዝደንቷን በማገዱ ናይጄሪያ ትዊተርን አግዳለች ያሉት ሚስተር ትራምፕ ለዚህም ሀገሪቱን እንኳን ደስ አለሽ ብለዋል፡፡ሌሎች ሀገራትም የናይጄሪያን ፈለግ በመከተል ትዊተርን ብቻ ሳይሆን ፌስ-ቡክንም እንዲያግዱ ትራምፕ ጠይቀዋል፡፡ትራምፕ ባወጡት መግለጫ ጥሩውን እና መጥፎውን ሊለዩ የሚችሉት እነርሱ ማናቸው ብለዋል፡፡

በስልጣን ላይ በነበሩበት ጊዜ ፌስ-ቡክ እና ትዊተርን ማገድ እንደነበረባቸውም በቁጭት ገልጸዋል፡፡ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ካስተላለፏቸው መልዕክቶች ጋር በተያያዘ በሁለቱም የማህበራዊ ሚዲያዎች የታገዱ ሲሆን ትዊተር እገዳው እስከመጨረሻው እንደሚጸና አስታውቋል፡፡

ፌስቡክ ደግሞ ቢያንስ ለሁለት ዓመታት ያክል ከታገዱ በኋላ የፌስቡክም የኢኒስታግራምም አካውንታቸው እንደሚመለስላቸው ገልጿል፡፡በሌላ በኩል የናይጄሪያ መንግስት ትዊትርን ማገዱን ተከትሎ በርከት ያሉ የሀገሪቱ ዜጎች መንግስት ላይ ክስ መመስረታቸው ተሰምቷል።

ግዙፉ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ትዊተር የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ የለጠፉትን ጽሁፍ ግጭት ቀስቃሽ ነው በሚል ከገጹ ማንሳቱ ይታወሳል፡፡

ዘገባው፡- የዘጋርዲያን ነው

ቀን 03/10/2013

አሐዱ ራድዮ 94.3

The post የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ናይጄሪያ ትዊተርን በማገዷ መደሰታቸውን ገለፁ፡፡ appeared first on አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን.

Source: Link to the Post

Leave a Reply