የቀድሞው የአብን ጽ/ቤት ኃላፊ እነ ጋዜጠኛ በለጠ ካሳ የሚያስተባብሩት “ዕውቀት ነፃ ያወጣል” የተሰኘው መፀሐፍትን የማሰባሰብ ዘመቻ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ።  አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሞማ…

የቀድሞው የአብን ጽ/ቤት ኃላፊ እነ ጋዜጠኛ በለጠ ካሳ የሚያስተባብሩት “ዕውቀት ነፃ ያወጣል” የተሰኘው መፀሐፍትን የማሰባሰብ ዘመቻ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሞማ…

የቀድሞው የአብን ጽ/ቤት ኃላፊ እነ ጋዜጠኛ በለጠ ካሳ የሚያስተባብሩት “ዕውቀት ነፃ ያወጣል” የተሰኘው መፀሐፍትን የማሰባሰብ ዘመቻ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሞማ ታህሳስ 19 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የቀድሞው የአብን ጽ/ቤት ኃላፊ እነ ጋዜጠኛ በለጠ ካሳ የሚያስተባብሩት “ዕውቀት ነፃ ያወጣል”መፅሀፍትን የማሰባሰብ አመቻ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገልጧል። የመፀሐፍትን ማሰባሰቢያ ማዕከላትም በአዲስ አበባ:_ ሀ) ሀሁ መፅሐፍት መደብር ቁጥር 1,ስቴዲየም ፊት ለፊት ናሽናል ታወር ምድር ወለል እና ቁጥር 2, ሜክሲኮ ቡናና ሻይ ፊትለፊት ደብረ ወርቅ ታወር ጎን መደብር 9A ለ) ኤዞፕ መፀሐፍት መደብር አራዳ ጊወርጊስ ከአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ከፍ ብሎ፣ ሐ) ብራና መፀሐፍት መደብር አራት ኪሎ ቅድስት ማርያም ከማኅበረ ቅዱሳን ሕንፃ ጎን፣ መ) አራት ኪሎ ምኒልክ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት መንገድ ላይ ለላቀውና ለሻረው መሆናቸውን አስተባባሪዎች አስታውቀዋል። ማንኛውም በጎ ፈቃደኛ ሰው በአቅራቢያው በሚገኙ የመፅሐፍት መደብሮች በመገኘት ስጦታውን ማበርከት እንደሚችል ተጠቁሟል። በተያያዘ ለወልቃይትና ለራያ አካባቢ ትምህርት ቤቶች እና ቤተ መጽሓፍት፣ መጽሓፍትን ገዝቶ በተጠቀሱት መደብሮች እና መቀበያ ቦታዎች ለማድረስ እንደሚቸገሩ ለገለጹ በጎ ፈቃደኞችም ለአሰራር ይመች ዘንድ የባንክ ሒሳብ ቁጥር ተከፍቷል። ይኸውም በበለጠ ካሳ እና ራውዳ አዲስ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000367860484 ሆኖ የተከፈተ መሆኑን አውቃችሁ ድጋፋችሁን እንድታደርጉ የዕውቀት ነፃ ያወጣል ዘመቻ አስተባባሪዎች ጠይቀዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply