የቀድሞው የአዴፓ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሃንስ ቧያሌው ከሰኔ 15ቱ የባለስልጣናት ግድያ ጋር በተያያዘ በአቃቢ ህግ ምስክርነት ቀርበው ቃላቸውን ሰጡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ታህሳስ 27 ቀ…

የቀድሞው የአዴፓ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሃንስ ቧያሌው ከሰኔ 15ቱ የባለስልጣናት ግድያ ጋር በተያያዘ በአቃቢ ህግ ምስክርነት ቀርበው ቃላቸውን ሰጡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 27 ቀ…

የቀድሞው የአዴፓ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሃንስ ቧያሌው ከሰኔ 15ቱ የባለስልጣናት ግድያ ጋር በተያያዘ በአቃቢ ህግ ምስክርነት ቀርበው ቃላቸውን ሰጡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 27 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም በአማራ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ ከተፈፀመው የግድያ ወንጀል ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው የታሰሩት የአዴሃን የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ስለሽ ከበደን ጨምሮ የጦር መኮንኖች እና የአማራ ልዩ ሀይል አባላት በባህር ዳር ማ/ቤት ከታሰሩ አንድ ዓመት ከ6 ወራት አልፏቸዋል። አቃቢ ህግ በሰኔ 15ቱ የአማራ ክልል ባለስልጣናት ግድያ ተጠርጥረው በእስር ላይ በሚገኙ የጦር መኮንኖች፣የአማራ ልዩ ሀይል አባላት እና በአዴሃን የውጭ ጉዳይ ኃላፊ በአቶ ስለሽ ከበደ ላይ ምስክሮችን ማሰማት ከጀመረ ሰነባብቷል። የአቃቢ ህግ ምስክር የሆኑት የቀድሞው የአዴፓ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሃንስ ቧያሌው ዛሬ ታህሳስ 27 ቀን 2013 ዓ.ም በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ቀርበው ቃላቸውን ሰጥተዋል። አቶ ዮሃንስ ቧያሌው ከሰጡት የምስክርነት ቃል መካከል በወቅቱ ኢመደበኛ አደረጃጀት እየተስተዋለ ነው በሚል ይገመግሙ እንደነበር፣ ሰኔ 12 ከፀጥታ ጋር በተያያዘ ምክትል ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን ባሉበት በአዲስ አበባ ግምገማ እንደነበር ተናግረዋል የሚለው ይገኝበታል። በተጨማሪም የሰለጠነው ልዩ ሀይልም ቀደም ሲል ሰልጥኖ ህዝባዊ አገልግሎት ሲሰጥ ከነበረው ጋር ሆኖ የሕወሓትን ጠባጫሪ እንቅስቃሴ ከመመከትና የህዝቡን ሰላምና ደህንነት ከማስከበር ውጭ የተለየ አላማ እንዳልነበረው ማስረዳታቸው ተገልጧል። ከአቶ ዮሃንስ ቧያሌው በተጨማሪም ኮንስታብል እንደሻው የተባሉ የአቃቢ ህግ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። በዚህም እስካሁን 69 የአቃቢ ህግ ምስክሮች ቃላቸውን ሰጥተዋል። የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ዳኞችም አቃቢ ህግ በተደጋጋሚ ምስክሮችን ስለምን አሟልቶ እንደማይቀርብ ጠይቀዋል፤ይህን ማድረግ ባለመቻሉም የተከሳሾች መብት እየተጣሰ ስለመሆኑ ተናግረዋል። አቃቢ ህግ በበኩሉ ሁኔታዎች አልመች በማለታቸው፣ በርካታ ምስክሮች በግዳጅ ላይ በመሆናቸውና የአድራሻ ለውጥ እያጋጠመው በመሆኑ አሟልቶ ለማቅረብ አለመቻሉን አስረድቷል። የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤቱም ለጥር 24 ቀን 2013 ዓ.ም ምስክሮችን አሟልቶ ይዞ እንዲቀርብ ሲል ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply