የቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክት ስንብት

https://gdb.voanews.com/022a0000-0aff-0242-ba45-08daece2a7c9_w800_h450.jpg

በብዙ አስር ሺዎች የተቆጠሩ የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ባለፈው ቅዳሜ ያረፉትን  የቤተክርስቲያኒቱ የቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክት በመሰናበት ላይ ናቸው።

የብጹዕነታቸው አስከሬን በቅዱስ ጴጥሮስ ቤተ ክርስቲያን ለስንብት የተቀመጠ ሲሆን በርካታ ምዕመናን ለሰዓታት ረጅም ሰልፍ ይዘው በመጠበቅ እየተሰናበቱ ናቸው።

ቤኔዲክት በስድስት መቶ ዓመታት ከካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያኒቱ መሪነት በገዛ ፈቃዳቸው የተሰናበቱ የመጀመሪያ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ናቸው። ህይወታቸው ከማለፉ በፊት የመጨረሻው ቃላቸው፣

 “ጌታዬ እወድሃለሁ” እንደነበረ የቫቲካን ዜና አመልክቷል።

በዘጠና አምስት ዓመታቸው ያረፉት የቀድሞው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አስከሬን በቤተ ክርስቲያኑ እስከፊታችን ረቡዕ ለስንብት ይቆይ እና የቀብር ሥነ ስርዓቱ ኅሙስ ዕለት እንደሚከናወን ተገልጿል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply