የቀድሞ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ በፈቃዳቸው ከኃላፊነታቸው ተሰናበቱ- ከመጋቢት 12/2016 ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን ለኮሚሽኑ አዳዲስ የአመራር ሹመቶች ተሰጡ። በበላይነት የሚመራዉ ቦርድም ተሰየመ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/B5qJEGFRpHqEmr7iN313NV_4lABshC5HFGW8oCm2mn_jw2Y3GpudLbJ1_LQlKWsop1XhXlasGJjf233RBzOwcs5ic8hlZcinepTN01i0qcvp9kSOAYU-YCNSV0bcwcBH_eVDsU3aNbI4iOha0lAZZHjAVgTNOjTgzbT7Bg3TGBYRzYPqB2zpUEUOxpVNVURv6dp7AnypPp8GJcziIdAzjIjp5KGZk7YdgTnw2RdF3vLdMSzht8T5C4vgevQsP2FD4fjt-2LrltyCD1Q51tCgZeCHp0G2aHLKq9qsdCYnb9DCUOfYS6OWrI62saw7H2tQ-Qaz2iIizIllTz6K8LtqrA.jpg

የቀድሞ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ በፈቃዳቸው ከኃላፊነታቸው ተሰናበቱ

– ከመጋቢት 12/2016 ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን ለኮሚሽኑ አዳዲስ የአመራር ሹመቶች ተሰጡ። በበላይነት የሚመራዉ ቦርድም ተሰየመ።

አቶ ተሾመ ቶጋ በግል ጉዳያቸዉ ምክንያት በኮሚሽነርነት ላለመቀጠል ያቀረቡት ጥያቄ በመንግስት ተቀባይነት በማግኘቱ የኮሚሽነርነት ቦታቸዉን ከመጋቢት 3/2016 ጀምሮ ለቀዋል።

በምትካቸዉ ከመጋቢት 12/2016 ጀምሮ አቶ ተመስገን ጥላሁን የብሄራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነዉ ተሹመዋል።
የኮሚሽኑ የሎጂስቲክስ እና አስተዳደር ዘርፍ ም/ኮሚሽነር በሆኑት በዶ/ር አትንኩት መዝገበ ምትክ አቶ ተስፋዓለም ይህደጎ ከመጋቢት 12/2016 ጀምሮ ተሹመዋል ።
በተጨማሪም ኮሚሽኑን በበላይነት የሚመራ በፍትህ ሚኒስትሩ በዶ/ር ጌድዮን ጢሞቲዎስ የሚመራ እና አምስት ከፍተኛ አመራሮች አባል እንዲሁም ኮሚሽነር ፀሀፊ የሆኑበት ቦርድ ተሰይሞለታል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

መጋቢት 13 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply