የቀድሞ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የቦርድ አባላት በማንኛውም የፋይናንስ ተቋማት አገልግሎት እንዳይሰጡ ታገዱ፡፡በንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ውስጥ ለተፈጠረው ችግር ተጠያቂ ናቸው ያላቸውን የቀድ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/Y-fKkKsQqpzKB-hbI1-KqmBVoHWMKb0XvRS4IgspxHvZk1BtXODWPFPjreSV12Fioe6ky9KHD4Snw5qMFhfTgxSbT1ukGziS67W6HJVB8PcyjYF9msYYoytPGPOZO2PBj3sYhgu-wVgIpqx2Sj-NVCdy0-eu6biAYDxDY5tYQ-jS37gXkXoo7ZKu5-fgzf2KyD1VZpwh-wunCGVlvVyn7gwhdbWRnWycLpVzify4S24PoqoeoR8V2S6t2QnIoQO8wHzlLr_zBByZRnzh18tvDsj7RCcSavND4WKDgekMlNiUD86Wci2qI8i1WFw5ZudHKOGuIHIOGzmqN0niIs4Zvw.jpg

የቀድሞ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የቦርድ አባላት በማንኛውም የፋይናንስ ተቋማት አገልግሎት እንዳይሰጡ ታገዱ፡፡

በንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ውስጥ ለተፈጠረው ችግር ተጠያቂ ናቸው ያላቸውን የቀድሞ 12 የቦርድ አባላት፣ በማናቸውም የፋይናንስ ተቋማት ውስጥ ግልጋሎት እንዳይሰጡ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዕግድ ጥሎባቸዋል፡፡

ብሔራዊ ባንክ ባለፈው ሳምንት ለ12ቱ የቀድሞ የቦርድ አባላት በጻፈው ደብዳቤ፣ ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ለገጠመው ችግር በጋራም ሆነ በተናጠል ተጠያቂ መሆናቸውን ባደረገው ምርመራ ማረጋገጡን በመጥቀስ፣ ከዚህ በኋላ ለስድስት ዓመታት በየትኛውም የፋይናንስ ተቋም ውስጥ እንዳይሠሩ ውሳኔ እንዳሳለፈባቸው አስታውቋል፡፡

በብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ የተጻፈው ደብዳቤ እንደሚያስረዳው፣ የንብ ባንክ የቀድሞ የቦርድ አባላት በማናቸውም የፋይናንስ ተቋማት በቦርድ ኃላፊነት፣ በዋና ሥራ አስፈጻሚነትና በተለያዩ የሥራ ኃላፊነቶች እንዳይመደቡ ወስኗል፡፡

የቀድሞዎቹን የቦርድ አባላት የሚተኩት አዲስ የተመረጡት የቦርድ አባላት ደግሞ ኃላፊነታቸውን ተረክበው ሰኞ ጥር 27 ቀን 2016 ዓ.ም. ሥራ መጀመራቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡(ሪፖርተር)

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥር 29 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast
Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply